Posts

Showing posts from July, 2022

ምዕራብ ፀሃይ መጥለቂያ እንጂ ህይወት መንጠቂያ አይደለም

ማሙሽና ቲሞ ማሙሽ፣ ምን እንደሚገርመኝ ታቃለህ? ቲሞ፣ ምን? ማሙሽ፣ ለምን ቲሞ እንደምንልህ? ቲሞ፣ ቲማቲም ባጭሩ ሲቆላመጥ ቲሞ ነው፡፡ ማሙሽ፣ ዛሬ ምን ብዬ ፖሰትኩኝ መሰለህ፣ ምዕራብ ፀሃይ መጥለቂያ እንጂ ህይወት መንጠቂያ አይደለም፡፡ ጥዋት ፀሃይ እየሞኩኝ እነ ማይካደራ፣ አበዱራፊ፣ መተማ፣ ቦርኒ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ጎቦ፣ ኮጎ ዳላ፣ ምናምን የሚኖሩ ወገኖቻችን ትዝ እያሉኝ ፀሃይ ሳትሰስት ለሁሉም ህይወት ለመሆን በምስራቅ ትወጣለች ክፉ ሰዎች በምዕራብ ህይወት ይነጠቃሉ አልኩና ለሰው አጋራው እልሃለው፡፡ ቲሞ፣ በጣም ያሳዝናል፣ ግንኮ መከላከያ ክፉዎቹን እያጨዳችው ነው፡፡ ሆን ተብሎ የብሄር ግጭት ለማስነሳት ኮ ነው፡፡ ማሙሽ፣ የብሄር ግጭት ለመነሳት የሚያስገድድ ነገር ሳይኖር መሆኑ እነዳልከው ሆን ተብሎ የሚሰራበት እና ሌላ ትርፍ ለማግኘት ነው፡፡ የራሱን ሰላማዊ ህይወት እየለፋ ከአካባቢው ጋር ተስማምቶና ተቻችሎ የሚኖር ዜጋ እንደዚህ አይነት ግፍ አይፈፀምበትም፡፡ እንኩዋን ኢትዮጵያ ሌሎች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያልዳበሩ ማህበረሰቦችም አያደርጉትም፡፡ ቲሞ፣ መንግስት ስራውን በትክክል እነዲሰራ ሰዉ ቢተባበር ጥሩ ነው፡፡ በተለይ እነዚህ ለምዕራብ ድንበር በቀረቡት ያገራችን ከተሞች፡፡ ማሙሽ፣ መንግስት እራሱ ለዚህ ጉዳይ በቂ ትኩረት ሰቶታል ወይ? አንዴ፣ ሁለቴ፣ሶሰቴ፣ ሲደጋገም የመንግስትን አካሄድ መጠራጠር እንዳይጀመር መጠንቀቅ ይበጃል፡፡ የሰው ደም ይጣራል፣ የስካሁኑ ይበቃል፡፡ ሃሳብን ሰብሰብ አድርጎ በቅን መንፈስ መፍትሄ እነዲመጣ ቀን ከሌት መልፋት ይጠበቅበታል መንግስት፡፡