እውነት ተማርካለች??



እንደወደደችህ ማወቅ ከፈለክ እነዚህ ምልክቶች መልስ አላቸው
ሴቶች በተፈጥሮ ስሜትን የመደበቅ ችሎታ አላቸው። ነገር ግን መቆጣጠር የማይችሏቸው እውነተኛ ስሜታቸውን የሚናገሩ የሰውነት ምልክቶች አሉ። አምስቱ ምልክቶች እነሆ፦


1. ዓይኖቿ፦ ሴቶች የሚወዱትን ሰው ሲያዩ የዓይናቸው የውስጥ ብሌን ሰፋ ብሎ ይታያል።
2. ደረትና ጡቶቿ፦ በተለይ በዛ ብላችሁ ጨዋታ ላይ ከሆናቹ ይህ ምልክት በጣም እርግጥ ይሆናል። ሴቶች         ደረታቸውን በተለይ ደግሞ ጡቶቻቸውን ወደሚማርካቸው ሰው አዙረው ይታያሉ። ስለዚህ ይህንን ምልክት ካየህ አትዘናጋ።

3. ፀጉሯን መነካካት፦ ሌላው መደበቅ የማትችለው ከማረካት ሰው ጋር ስታወራ የሚሰማት የደስታ ስሜት በፀጉሯ እንድትጫወት ያደርጋታል። ስለዚህ በሚቀጥለው ስታወሩ ፀጉሯን በየመሃሉ ስትነካካ ካየሀት መፍጠን አለብህ።

4. የሰውነት እንቅስቃሴህን ትኮርጃለች፦ ለምሳሌ ከንፈርህን ነከስ ስታደርግ ወዲያው እሷም ከደገመችው ወይም እጅህን ስታጣምር ወዲያው ተከትላህ ካጣመረች እንዲሁም ሌሎች የሰውነት እንቅስቃሴህን ከደገመችው ተስፋ አለህ፣ በጣም።

5. ዝም ብላ ትስቃለች፦ ምንም እንኳን ቀልድ ባትችል ትንሽ ስትሞክር እንኳን እስኪገርምክ ከሳቀች ጥርጣሬ አይግባህ ተማርካለች ማለት ነው።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!