የዓለማችን ቁንጮ ባለፀጎች 2019 እ.ኤ.አ.
የዓለማችን ቁንጮ ባለፀጎች
በፈሰንጆቹ ማርች 6,2019 ፎርብስ መፅሔት የወቅቱን የመጀመሪያ ባለፀጎችን አውጥቶ ነበር። ፎርብስ እንዳለው ‘ ካፒታሊዝም እየተመታ ነው’ ብሏል። ምክንያቱ ደግሞ ‘ከ10 ዓመት በኋላ ለሁለተኛ ተከታታይ አመት የቢሊየነሮቹ ኅብት ከመቀነሱም በላይ የቢሊየነሮቹ ቁጥርም ቀንሷል። እስኪ ስድስቱን ቁንጮ ባለፀጎች እንይ፦
1. ጄፍ ቤዞስ እና ቤተሰቡ፦
የኢንተርኔት ንግድ መረቡ አማዞን መስራች የሆነው ጄፍ ቤዞስ በዚህ ዓመት ብቻ ኅብቱ በ19ቢሊየን ዶላር ጨምሮ 131 ቢሊየን ዶላር ሆኖ አንደኛ ቢሆንም ከ 25 ዓመት ትዳር በኋላ ሚስቱ ማኬንዚ ለፍቺ ስላመለከተች ኅብቱን እኩል ሊካፈሉ ይችላሉ። ከተፋቱ ማኬንዚ የሴቶች ቁንጮ ቢሊየነር መሆኗ አይቀርም።
2. ቢል ጌትስ፦
በ6.9 ቢሊየን ዶላር በዚህ ዓመት ብቻ ኀብቱ የጨመረው ቢል ጌትስ በ 96.5 ቢሊየን ዶላር ሁለተኛ ነው። ቢልና ሚስቱ ሜሊንዳ የዓለማችን ግዙፍ የግል የዕርዳታ ተቋም ይመራሉ። ቢል ጌትስ ማይክሮ ሶፍት ውስጥ 1% አካባቢ ሼር ብቻ ቢኖረውም በተለያዩ የንግድ ደርሻዎች ውስጥ ባለቤት በመሆንና ንብረቶች ላይ ገንዘብ በማኖርም ይሰራል። ቢል ጌትስ እስከ አሁን ለቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የዕርዳታ ድርጅት 35.8 ቢሊየን ዶላር ሰጥቷል።
3. ዋረን በፌት፦
የቢል ጌትስ የቅርብ ጓደኛ ዋረን በፌት ኀብቱ በ 1.5 ቢሊየን ቀንሶ በ 82.5 ቢሊየን ዶላር ሶስተኛ ነው። 99% ኀብቱን ለዕርዳታ ድርጅት እሰጣለው ብሎ ቃል የገባው ዋረን በፌት ከ60በላይ ድርጅቶች ሲኖሩት እስካሁን ለነ ቢል ጌትስ የዕርዳታ ድርጅት 3.4 ቢሊየን ብር ለግሷል።
4. በርናርድ አርናውልት፦
ፈረንሳዊው በርናርድ ከ 70 በላይ ብራንድ(የተመዘገበ የንግድ ስም) ባለቤት ሲሆን 76 ቢሊየን ዶላር አለው።
5. ካርሎስ ስሊም ሂሉ፦
የደቡብ አሜሪካው መሪ የቴሌኮም ድርጅት አሜሪካ ሞቪል ባለቤት ሲሆን 64 ቢሊየን ዶላር አለው።
6. አማንቺዎ ኦርቴጋ፦
የዛራ ፋሽን ባለቤት ሲሆን በተለያዩ ንግዶች ላይም ይሳተፋል። በዓመት ከደሮጅቶቹ ባለቤትነት የትርፍ ክፍያ ብቻ በዓመት 400 ሚሊየን ዶላር ያገኛል። በዓለም ላይ ከ7,500 በላይ የንግድ ቤቶች ሲኖሩት 63.3 ቢሊየን ዶላር አለው።
Comments
Post a Comment