እንኳን አደረሰን፤ ማርች 8


የዛሬውን የሴቶች ቀን፤ በስኬታማ ሴቶች
ታዋቂው መፅሔት ፎርብስ ያቸፈው አንድ አመት የመጀመሪያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ካላቸው ሴቶች ውስጥ የመጀመሪያዎቹን አምስት እነሆ፦
5. አብጌይል ጆንሰን

 የፊደሊቲ ካምፖኒ አስተዳዳሪ ሆና የተሾመችው አቢጌይል በአምስተኛ ተቀምጣለች። በዓያቷ የተቋቋመው ይህ ድርጅት በተለያዩ የፋይናንስ ኢንቨስትመንት፣ በኢንሹራንስና ኤሌክትሮኒክስ ንግድ ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን በዓመት ከ18 ቢለየን ዶላር በላይ ገቢ ያስገባል።
4. ሜሪ ባርባራ

የመጀመሪያ ሴት የመኪና አምራች ድርጅት አስተዳዳሪ ሆና የተሾመችው ከ አራት ዓመት በፊት ነው። የምታስተዳድረው ጀነራል ሞተርስ በስድስቱ አህጉራት አራት መቶ የሚጠጉ ማምረቻ ያለው ሲሆን በ ዓመት ወደ 10,000,000 መኪኖች እያመረተ 145 ቢሊየን ዶላር አመታዊ ገቢ አለው።
3. ክርስቲያን ላጋርዴ

አለም አቀፋን የገንዘብ ተቋም የምታስተዳድረው ላጋርዴ ትልልቅ የፋይናንስ ውሳኔ ሰጪነታቸው የታወቁ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2011ዓም ከተመረጡ በኋላ እስካሁን እያገለገሉ ይገኛሉ።
2. ቴሬሳ ሜይ፦

የእንግሊዝ ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ የሆኑት ቴሬሳ ሜይ፣ እ.ኤ.አ. ከ2016 ጀምሮ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስቴር ናቸው።
1. አንጌላ ሜርክል፦

 የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ማህበር መሪ ሲሆኑ እ.ኤ.አ ከ 2005 ጀምሮ የጀርመን ቻንስለር ናቸው። በኳንተም ኬሚስትሪ ዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ሜርክል ፖለቲካውን መቀላቀል የጀመሩት እ.ኤ.አ. በ 1989ዓም ነው። ፎርብስም ያለፈው ዓመት ቀዳሚ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴት ብሎ መርጧቸዋል

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!