በፍቅር ግንኙነት መሪ መሆን ትፈልግያለሽ፤ ማርች 8



በሴቶች ቀን ለሴቶች ብቻ
ባለቤትሽን ወይም ጓደኛሽን በቁጥጥር ስር ማድረግ ትፈልጊያለሽ? ማለቴ የሰመረ ግንኙነት ነገር ግን አንቺ የምትመሪው? ብልኀትሽን በመጨመር እነዚህን አስራ አምስት ድርጊቶች ፈፅሚ። ከዛም ውጤቱን ታካፍይናለሽ።
ትዳር ላይም ይሁን በጓደኝነት ላይ ያለ ፍቅር የአንድ ወገን ኀላፊነት ብቻ እንዳልሆነ እሙን ነው። ነገር ግን በብልኀት እንዲመራ ላንቺ የተወሰኑ ምክሮች ለመለገስ ያህል ነው፤ ማርች 8 አይደለም እንዴ።

1. ፍቅርሽን ግለጪ፦ ሁል ጊዜም እንኳን ባይቻል በተለያዩ መንገዶች ፍቅርሽን መግለጥ ለምሳሌ በመሳም በመኮርኮር የሚወደውን ምግብ በማቅረብ በመሣሠሉት።
2. በግልፅ መነጋገር፦ የግንኙነት ፀር የሆነውን መደባበቅ ለማስወገድ ጥረት አድርጊ።
3. ድጋፍ ስጪው፦ በስራውም ይሁን፣ በ መዝናኛው እርዳታሽ የሚያስፈልገው ሆኖ ከተሰማሽ ደግፊው። መቼም ሰው ሚደገፈው ችግር ሲመጣ ብቻ መሆን የለበትም።
4. ከፍቅረኛም የቅርብ ጓደኛው ሁኚ
5. አክብሪው፦ ይሄንን ስልም የራስሽንም ክብር ግን ማስጠበቅ አለብሽ።

6. የሚስበው ነገር እንዲስብሽ ጥረት አድርጊ፦ በሁሉም ባይሆን እንኳን ለምሳሌ የሚወደው የቀለም አይነት ካለ አንቺም እንደምትወጂው አሳውቂው።
7. የብቻ ጊዜ ስጪው፦ ወንዶች እንደሴቶች ስላልሆኑ የማሰቢያ ጊዜና ቦታ በየጊዜው መፈለጋቸው አይቀርምና ፍላጎቱን አክብሪለት።
8. ከልብሽ አድምጪው
9. አሞግሺው፦ ከጊዜ ጊዜ ሙገሳ ለግሺው ይህም የበለጠ ፍላጎትሽን ለሟሟላት ኀይል ይሆነዋል።
10. አትጨቃጨቂ፦ በሆነው ባልሆነው ጭቅጭቅ አትፍጠሪ፣ የሚያጨቃጭቅ ነገር ቢመጣም ከመጨቃጨቅ ጊዜ ሰታችሁት በሌላ ግዜ እንድትነጋገሩበት አመቻቺ።

11. ታማኝ ሁኚ፦ ታማኝ መሆኑንም ማረጋገጥ አትዘንጊ።
12. እውነተኛ አንቺን ሁኚ፦ ፍቅራችሁ ዘልቆ እዚህ ከደረሰ በኋላ ማስመሰሉ ይጎዳሻል እንጂ ጥቅም የለውም ስለዚህ ራስሽን ሁኚ ሁልጊዜም።
13. ደስታሽን ከልብሽ አጋሪው
14. አልፎ አልፎ የራስሽን ኘሮግራም ይዘሽ የምትወዱት ስፍራ ጋብዢው።
15. በአልጋ ላይ አዳዲስ ነገር አሳይው።
ፍቅር ሰቶ መቀበል ነው። እነዚህን በመስጠት የምትቀበይው ግን እጅግ እጅግ ብዙ እንደሚሆን ጥርጥር አይግባሽ።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!