ማነው ባለጊዜ?


ማነው ባለጊዜ?
ለሁላችን እኩል ጊዜ ነው ያለን በቀን፣ በወር ወይም በዓመት። ማነው ባለጊዜ ብሎ ጥያቄ አለ እንዴ ካላችሁ ‘አዎ አለ’ እላችዋለሁ። ‘ እንዴት?’ ለምትሉ እንደሚከተለው መልስላችዋለው።

ብርሃኑ በጣም ታታሪ ሰራተኛ ነው። እያንዳንዱን የዕለት ውሎ በሚገባ ኘላን ስለሚያደርግ ጊዜ የለውም። 8 ሰዓት ይሰራል፣ 2ሰዓት ያህል ይማራል፣ ያጠናል፣ ይተኛል የመሳሰሉት። የሚሰራበት መስሪያ ቤት ሀያ ሰራተኞች ሲኖሩት ምርታማና ስኬታማ ነው። አቶ ኃይሉ የእንጨት መሰንጠቂያ ድርጅት ሲጀምሩ እሳቸውና አንድ ለጊዜው የቀጠሩት ጉልበት ሰራተኛ ነበረ። አሁን እሳቸው በሁለት ወይም ሦስት ቀን አንዴ ብቅ እያሉ ሰራተኞችን ያበረታታሉ። የብርሃኑና የስራ ባልደረቦቹ ስምንት ሰዓት ሲደመር 160 የስራ ሰዓት አላቸው። ማነው ባለጊዜ?

እዬብ የሚባል የሰፈሬ ልጅ አለ። የተወሰኑ ወንድሞቹ ከአገር ውጪ ይኖራሉ። እነሱ በሚረዱት ብር ብቻ ተወስኖ ቀኑን ሙሉ በችግር ይኖራል። ስራ ለመስራት በቂ አውቀት የለውም እንዲኖረውም አይጥርም። ሲሳይ የባንክ ሰራተኛ ሲሆን ጠዋት ወቶ ማታ ይገባል። በወር 30,000.00 ብር ደሞዝ ስላለው በዛው ቀን 1,000.00 ብር ተከፍሎት ከወንድሙ እዬብ ጋር ቃና ቲቪን አብረው ያያሉ። ማነው ባለጊዜ?

በሰሚራና በመሀመድ መካከል ከፍተኛ ፉክክር አለ ፉክክሩም የአባታቸውን የአስመጪነት ንግድ ለመምራት ነው። ውሳኔው የአባታቸው ቢሆንም የሚያመጣውን ጥቅም በማሰብ የቤተሰቦቻቸውን አባላት ሁሉ ተሳትፎ እየጠየቁ ነው። መሀመድ ቤተሰቡ ላይ በማተኮር ብዙውን ጊዜ እነሱ ጋር እያሳለፈ ነው። ሰሚራ ግን ጊዜ ስለሌላት ከአባቷ ጋር ሱቅ ታሳልፋለች። ማነው ባለጊዜ?

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!