ልብሴን አትንኪ!!
ባለፈው ሳምንት ጓደኛዬ የራት ግብዣ ኖሮባት የምትወደውን የራት ልብስ ለመልበስ ስትሞክር ቆሽሾ ታገኘዋለች ያቆሸሸችውም እህቷ ለብሳው እንደሆነ ነገረችኝ። ትንሽ ተናዳ ስለነበረ አሳዘነችኝና ለወደፊቱ መፍትሔ ይሆናት ዘንድ ይህንን እንድታነብ ጋብዣታለው። በተለይ የሰውነት አቋማቹ ሲመጣጠን ችግር እንደሆነ አምናለው።
ወንድሜ ወይም እህቴ ልብስና ጫማዬን ሲዋሱ ያናደኛል ካላችሁ የሚከተሉትን ምክሮች ተግብሩ።
• መዋዋሥ ያለ ነው፦ እንኳን ወንድም ወይም እህት ሆኖ ከሩቅ ጓደኛም መዋስ ያለ ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው ምርጫ ይህን መቀበል መሆን ይችላል።
• መናገር፦ እንደወንድም ወይም እንደ እህት ልብሳቹን ወይም ጫማቹን እንዳይለብሱ በግልፅ መናገር። ነገር ግን በሰከነና በጥሩ ሁኔታ ማስረዳት።
• ተመሳሳይ መግዛት፦ ወደድ ያለ ምርጫ ቢሆንም ለራሳቹ ስትገዙ ለወንድማቹ ወይም እህታቹም ተመሳሳዩን መግዛት መፍትሄ ከመሆኑም በላይ የወንድምነት ወይም እህትነት ፍቅራቹንም ያጠነክራል።
• መቆለፍ፦ መቼም በጣም ራስ ወዳድ ሆነን ልንታይ ብንችልም የመጀመሪያዎቹ ሦስት ምርጫዎች አልሰራ ካሉ አማራጩ ወይ ክፍላችንን ወይም ደግሞ ሳጥናችንን መቆለፍ የሚያዋጣ መፍትሔ ነው።
Comments
Post a Comment