የባህል ልብሳችን ቻይና ይመረታል እንዴ?
የባህል ልብሳችን ቻይና ይመረታል እንዴ?
የሃገራችን የባህል ልብሶች እጅግ የሚያምሩ እንደሆኑ በዓለም ከተመሰከሰላቸው ቆይቷል። የሃገራችን ጎበዝና ታታሪ ሸማኔ የሠራው ሸማ በጥንካሬም ሆነ በውበት እጅግ የተዋጣለት ነው። አሁን አሁን ደግሞ የፈላጊው ቁጥር ሲጨምር የድካሙን ዋጋ ያገኛል ሲባል የተለያዩ በተለይ ከቻይና የሚመጡ ሸማ መሣይ ጨርቆች እንዲሁም በእጅ የሚሰራውን ጥለት የሚያስመስሉ ኢምብሮደሪ ማሽኖች ሃገር ውስጥም ውጪም ስለሚገኙ ገበያው አስቸጋሪ ሆኗል።
መቼም በሸማኔ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ቆንጆ ሸማ የሠራው ልብስና በእጅ በጥንቃቄ የተሰራ ጥለት ያለው የባህል ቀሚሳችን በሙሉ በማሽን ለገበያ አዋጭነት ብቻ ከተሠራው ጋር መለያየት አለበት። ከዚህ በታች በ ኢንተርኔት እነዚህን የባህል ልብሶች ከሚሸጡ ያውጣጣዋቸው ናቸው። የትኛው እንደሚመች መምረጥ ነው።
Comments
Post a Comment