የልብ አድርስ ስጦታ!
ለፍቅረኛህ የምትሰጣት ውብ ስጦታ
ፍቅረኛህ እንደምታስብላትና እንደምትወዳት ከሚያሳውቁ ተግባሮች አንዱ ለስጦታህ የምትሰጠውን ትኩረት ነው። የሴት ልጅን ከሚማርኩ የስጦታ ዓይነቶች አስሩ እነሆ፦
1. ዘና ፈታ የሚያደርጓት ነገሮች፦ ለምሳሌ ቸኮሌት፣ የሻማ ስጦታ፣ ለስላሳ ሶፍት የመሣሠሉት።
2. ስስና ምቹ የለሊት ልብስ፦ የምትወደው ከለር ቢሆን ይመረጣል።
3. ቤቷ ስትሆን ምን ያህል እንደምትወዳት የሚያስታውሳት፦ ለምሳሌ የራስጌ መብራት……
4. ስትኳኳል የምትለብሰው ሻርኘ፦ ስትኳኳል ኦላዮዋ ላይ ጣል የምታደርገው በምትወደው ከለር
5. ጥሩ ሽታ የሚፈጥር፦ የቤት ፍሬሽነር፣ የመሣሠሉት የሚያምር ዲዛይን ይመረጣል።
6. የታቀደ የሽርሽር ፓኬጅ ትኬት፦ ከተማውስጥም ይሁን ወጣ ያለ በጉጉት የምትጠብቀው ይሁን።
7. ሴት ሴት የሚሉ ነገሮች፦ የሚያምሩ የሴት ካልሲዎች፣ የእጅ አምባር፣ የምትወደው ሻምፖኝም….
8. የተለያዩ መዋቢያ የያዘ ፓኬጅ፦ አምሮ የታሸገ ሆኖ መዋቢያ ነገሮችን የያዘ ፓኬት።
9. ያማረ የቦርሳ ውስጥ መስታወት።
10. ሽቶ፦ ውድ ሽቶ የማይወድ የለምና እሱም አማራጭ ነው።











Comments
Post a Comment