ያለሜካኘ? አይደረግም!
ሜካኘ ያልተጠቀመችው ሞዴል ተብጠለጠለች
የዛራ ፋሽን ቻይናዊዋ ሞዴል በቅርቡ ለድርጅቱ በተነሳችው የማስታወቂያ ፎቶ ምክንያት የሶሻል ሚዲያ መነጋገሪያ ሆናለች። ሞዴሏ በፎቶው ላይ ምንም ሜካኘ ባለማድረጓ ‘ ያስጠላል’ የሚል አስተያየት ሁሉ እያስተናገደች ነው።
ይህ አስተያየት እየተሰጠባት ያለው ዛራ የተለያዩ ፎቶዎችን በቻይናው ማህበራዊ ድረ ገፅ ዊቦ ላይ ከለቀቀ በኋላ ነው። ፎቶዎቹ የ 25 ዓመቷ ቻይናዊ ሞዴል ጂንግ ዌን ነው። ፎቶዎቹ የዛራን የተለያዩ አዳዲስ ሊኘስቲኮች የሚያስተዋውቁ ናቸው።
አስተያየት ሰጪዎቹም በግማሽ የዛራ ድርጅትን ለ ጂንግ ዌን ተፈጥሯዊ ውበት ክብር መስጨቱን ሲያደንቁ የተወሰኑት ደግሞ ‘ የምስራቆችን መልክ ለሚንቁ ዘረኞች እየተመቸ ነው ዛራ’ ብለዋል።
‘’ ይቅርታ እኛ ቻይናውያን ፊታችን ላይ ጠቃጠቆ የለንም’ የአንዷ አስተያየት ተፅፏል።
‘ ይህ ማስታወቂያ ውድቀት ነው።’ ሌላ አስተያየት።
ቢያንስ ፋውንዴሽን እንኳን አለመቀባቷ የገረመው የሚመስል አስተያየት ደግሞ ‘ የምር መጥቼ ፖውደር ልቀባት?’ ይላል።
በተቃራኒው ደግሞ ሌሎች አስተያየቶች ተፅፈዋል። ‘ የሰው የውበት አስተያየት ይለያያል’ ይላል አንድ አስተያየት ከዛም ይቀጥልና ‘ በኔ አስተያየት ጂንግ ዌን ያለ ሜካኘ ቆንጅዬ ናት’ ይላል።
የዛራ ፋሽን ተወካዩ ሲናገር የማስታወቂያ ፎቶዎቹ ለቻይና ብቻ አይደለም የሚሰሩት ለዓለም ሁሉ ነው ካለ በኋላ በስፔን፣ የዛራ ፋሽን ዋና መቀመጫ፣ ሁሉም ሞዴል በተፈጥሯዊ መልኩ ነው የሚነሳው። ስለዚህም የ የጂንግ ዌን የማስታወቂያ ፎቶ ሜካኘ ወይም ፎቶሾኘ ኤዲት የለውም ብሏል።
በመጨረሻም ሞዴሏ ስትጠየቅ ‘ ልጅ እያለው የፊቴን ጠቃጠቆ በጣም ጠላው ነበር ምክንያቱም አብዛኛው ቻይናዊ የለውምና’ ካለች በኋላ ‘ ሁለተኛ ደረጃ ስማር ሁሌም በሜካኘ እየሸፈንኩ ነበር ትምህርት ቤት የምሄደው፣ አሁን ግን እንደዛ አይሰማኝም እንደውም ጠቃጠቆዎቼን ወዳቸዋለው ብላለች።




Comments
Post a Comment