ከሷ ተማሩ


ጓደኛዬ፤ አታስመስይ እስኪ

ጓደኛዬና የፍቅር አጋሯ መሬት አይንካሽ አይንካህ ይባባላሉ፣ ለችግሯ በሙሉ መፍትሄ ይፈልጋል፣ ቀኑን እንዴት እንደምታሳልፍ ሃሳብ ያቀርባል እሷም በበኩሏ ኑሮዋም ሆነ ዓላማዋ እሱን ለማስደሰት፣ እንደምትወደው ለሁሉሞ ማሳወቅ ብቻ እንከን የለሽ የሆነ ግንኙነት አላቸው።
ነገር ግን ከወር በፊት ለሁለት አመት የዘለቀው ፍቅራቸው በማይመለስ መልኩ ተቋጨ። እንዴ ወደፊት ቢመለሱስ ካላችሁኝ ለምን እንዳለቀለት በስነልቦና አጥኝዎች ዘንድ የሚታወቀውን የሰው ልጅ ግንኙነት የተሳካና ዘላቂ የሚሆንበት ወይም ጊዜያዊና ደስታ የራቀው የሚያደርጉትን ምክንያት እየጠቀስኩ ላስረዳ።

ፍቅራቸው ያስቀናል የሚባሉ ጥንዶች ወይም ቤተሰብ ወይም ጓደኞች ከላይ የጠቀስኳቸው ጓደኞቼ ያላቸው አይነት ግንኙነት ሲኖራቸው ይመስለናል በጥቂቱም ቢሆን። ሆኖም በተመራማሪዎቹ እንደሚባለው እንደውም ያሳዝናል ምክንያቱም ከጊዜ በኋላ እውነታ ሲታወቅ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። እስኪ ከላይ ጓደኞቼን በምሳሌ እንይ።
መሬት አይንካሽ፦ በተፈጥሮ ህግ መሬት ሳትይዝ አትኖር፣ መቼም በጣም አልፎ አልፎ በጥሩ ሁኔታ መንከባከብ ያስደስታል። ስራ መሆን ግን የለበትም እስከመቼ ይችለዋል።
የችግሯ መፍትሄ ሁሉ በርሱ በኩል፦ እንኳን ለሚያፈቅሩት ሰው ለማይታወቅ ሰውም የችግር መፍትሄ መሆን በጣም ጥሩ ነው። ነገር ግን የእርሷ ጉዳይ ሁሉ የኔ ነው ካለ በሁለት መንገድ ግንኙነቱን ይጎዳል። መጀመሪያ የራሱን ችግር በትኩረት ከመፍታት ይስተጓጎላል ሁለተኛ በጣም ቀናተኛ ይሆናል። ስለዚህ የችግር መፍትሄ ሲሆን ወዶና ደስ እያለው ቀጥሎም ምንም ምላሽ ሳይጠብቅ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ትዳር ላይ ነበሩ።

ዓላማዋ እሱን ማስደሰት ብቻ፦ የሰው ልጅን ስሜት ሁልጊዜ አንድ አይነት ማድረግ አይቻልም። ተፈጥሮ ስሜታችን እንዲለዋወጥ በውስጡም አንድንማር እንድንለወጥ ታስገድዳለች ስለዚህ ጓደኛዬ ከዚህ ጋ እየተቃረነች ነው ማለት ነው። ደስ ሳይለው ስታይ እራሷን ልትወቅስ እሷን ከፍቷት እሱ ደስ ሲለው ያልተፈለገች እንዲመስላት ሆኗል ማለት ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ ስሜቱ ተለዋዋጭ እንኳን ሌላ ሰው ባለቤቱ ሰውዬው እንኳን በቅጡ ማይቆጣጠረው ስለሆነ ባትሞክረው ጥሩ ነበር።
ሁሉም ይይልኝ፦ ሰው እንዲያይላት የሞትፈልገው እንድትደነቅ ወይም ለማስቀናት ወይም ደግሞ ሌላ የምታሳየው ነገር ስለሌላት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በፌስ ቡክ በየቀኑ ማለት ይቻላል የነሱን ፎቶ ሳናይ አንውልም፣ ስንገናኝ የምታወራልን ከእርሱ ጋር ያደረጉትን በመደጋገም ጭምር ነበር ወሬዋ። ግንኙነቱ የነርሱ ብቻ፤ ሰው ቢያውቅም ባያውቅም ትርጉም ሊኖረው አይገባም ነበር። እሷ ለምሳሌ አንዷ ጓደኛችን እንኳን ያድናቆት ቃል ካልተናገረች ትጠምዳታለች። የሚያስከፋ አስተያየት ቢሰጥማ የሚፈጠረውን ሳሉት። ይህ ለማስመሰል የሚደረግ ድርጊት የማህበራዊ ህይወት ሁሉ የሚጎዳ ነው። ስለዚህ በልክ አድርጋው የሆነውን ሁሉ ለኛ ለማሳወቅ ከመጣር ይልቅ ለራሳቸው ግንኙነት ጊዜ ብትሰጥ ኖሮ እላለው።
እነዚህ ጉዳዬች ለፍቅር ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ቅድም እንዳልኩት ቤተሰብም፣ ማህበረሰብም በግኑኘቶች ላይ የማይጨበጡ ወይም ደግሞ መቆጣጠር የማንችላቸውን ነገሮች የግንኙነት መሰረት ማድረግ የለብንም። የምንችለውንም ስናደርግ ለሚደረግለት ሰው ኀላፊነት ሰጥተን በተጨማሪም ከልባችን ደስ ብሎን ብናደርግ የወደፊቱ ግንኙነት በፅኑ ፍቅር የታጀበ ይሆናል።

በነገራችን ላይ ጓደኛዬ አሁን ሌላ ጓደኛ ጋር ግንኙነት ጀምራለች። ብነግራት ከልቧ ስለማትሰማኝ ከዚው እንድታነብ አደርጋታለው። ይኸውልሽ የምታደርጊውም ይሁን የምታደርጊለት ነገር ከልብ የመነጨ ለግንኙነታችሁ ሁለታችሁም ኅላፊነት እንዳለባችሁ እንጂ የግል ስሜታችሁም ጉዳያችሁ የግላችሁ ነው። ለማስመሰል ወይም ኀላፊነትን ሰው ላይ በመጫን ከዛም ከህሊና ወቀሳ ለመዳን ደግሞ እሱ አለልኝ ወይም እሷ አለችልኝ እያሉ ከኅላፊነት መደበቅ አያዋጣም። መፋቀር የሚደረጀው ሁለታችሁም ህይወት ላይ ጠንካራ ሆናችሁ ማስመሰልን ወደ ጎን የተዋችሁ ጊዜ ነው።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!