ከሰው እኩል ህጋዊ መብት ይሰጥ ይሆን?
የኒውዚላንዱ ወንዝ የሰብዓዊ መብት ተሰጠው
ባለፈው ዓመት የኒውዚላንድ ፓርላማ ዋንጋኒዩ ለተባለው ወንዝ ከነገባሮቹ ለሰው የተሰጠውን ያህል መብት፣ ኀላፊነትና ግዴታ ሰቶታል። የፓርላማው ቃል አቀባይ ሲናገር ‘ ወንዙ ከተራራ ሰንሰለት ተነስቶ ብዙ መንገዶችን አቋርጦ ወደ ባህር የሚገባ ህይወት ያለው ነገር ነው’ ብሏል። ‘ በተጨማሪም 30 ሚሊየን የኒውዚላንድ ዶላር ለወንዙ ጥበቃና እንክብካቤ ተመድቧል’ ሲል ነው ያስታወቀው ቃል አቀባዩ።
የቦሊቪያ መንግስት ‘ የእናት ምድር የመባዛት፣ የውሃ፣ የንፁህ አየር፣ እንዲሁም የመጠበቅ መብት’ በሚል ህግ አፅድቋል። ህንድ፣ ኮሎምቢያ፣ ባንግላዲሽ የመሳሰሉት አገሮችም የተፈጥሮን ህጋዊ መብት ለማፅደቅ ዴር የደረሱ ናቸው። እንደ አንድ የህግ ምሁር አባባል ‘ ከሰጅም ግዜ በኋላ ዓለማቀፍ ይዘት ያለው የህግ ድንጋጌ እንቅስቃሴ እያየን ነው’ ብሏል።
እንግዲህ እንስሶችና ተፈጥሮ መብት ከተሰጣቸው ሊከሰሱም ሊከሱም ይችላሉ ማለት ነው። በአሁኑ ሰዓት በተለይ እንስሳት ጥፋት ቢያደርሱም በህግ አይጠየቁም ነገር ግን በድሮ ግዜ በአውሮፓም ይሁን በሌሎች አገሮች በህግ ይጠየቁ ነበር። የተወሰኑትን እንያቸው፦
• የባሰሉ ጉዳይ፦ አውራ ዶሮ በ ጀርመኗ ባሰል ከተማ የሰይጣን ጭፍራ የሆነ ድራጎን የሚፈለፍል እንቁላል በከተማችን በየቦታው እየጣለ ነው ብለው በ1474ዓም ዶሮውን ከሰውት ነበር።
• ተኩሎቹ፦ ቀን ቀን ሰው ማታ ማታ ተኩላ ይሆናሉ ብለው የፈረንሳይ ኗሪዎች በ16ኛው ክ/ዘመን ተኩሎችን ፍርድ ቤት ያቆሙ ነበር።
• ጦጣው ናሩቶ፦ በ2015ዓም የእንስሳት መብት ተሟጋቾች ለጦጣው ጠበቃ ቀጥረው ዴቪድ ስሌተር የተባለ ግለሰብ ከሰው ነበር ነገር ግን ጦጣው የመክሰስ መብት የለውም ብሎ ፍ/ቤቱ ክሱን ውድቅ አድርጎታል።
የናሩቶ ሰልፊ
• ከመርከብ የተረፈው ጦጣ፦ በእንግሊዝ ሃርትፑል ከተማ በናፓሊዩን ዘመን አንድ የፈረንሳይ መርከብ ከአለት ጋር ተጋጭቶ ይሰምጣል። በመርከቡ ላይ የነበሩት ሁሉ ሲሞቱ የፈረንሳይ ወታደር ልብስ የለበሰ ጦጣ ብቻ ይተርፋል። ጦጣውን ለሃርት ፑል ከተማ ፍ/ቤት የከሰሱት የፈረንሳይ ሰላይ ነው ብለው ነበር። ፍርድ ቤቱም ጦጣውን ጥፋተኛ ነው ብሎ በስቅላት እንዲቀጣ አድርጎታል።






Comments
Post a Comment