ያማረ እግር በቀላሉ
ያማረ እግር እንዲኖርሽ የግድ መዋቢያ ሳሎን መሄድ የለብሽም። እነዚህን መንገዶች ተግባራዊ ማድረግ በቂ ነው። በትንሽ ጥረት እና ጊዜ ብቻ።
1. የጥፍር ቀለም ሙሉ ለሙሉ ይልቅ፦ አሴቶን ያላቸው ማስለቀቂያ አትጠቀሚ። ቀለሙ ከለቀቀ በኋላ ጥፍሮችሽን ለመቃኘት የረዳሻል። አልፎ አልፎም ጥፍር ቀለም አትጠቀሚ። ይህን ማድረግሽ ጥፍርሽ እንዳይጠቁር ይረዳሻል።
2. እግሮችሽን ዘፍዝፊ፦ እግርሽን ለብ ባለ ውሃ ውስጥ ከ15-20 ደቂቃ ዘፍዝፊው። በዛውም ካገኘሽ የመዋቢያ ጨውና የወይራ ዘይት ማድረግ ተዓምር ያሳይሻል። እግርሽን ከማውጣትሽ በፊት ጥፍሮችሽን በስስ ጥርስ ብሩሽ ቦረሽ ቦረሽ አድርጊው።
3. በሻካራ ድንጋይ ማሸት፦ የእግርሽን ተረከዝና የታችኛው ክፍል በደንብ ማሸት። ይህም የሞቱ ሴሎችን ስለሚያስለቅቅ ቆዳሽ እንዳይሰነጣጠቅ ያደርገዋል። ይህን ምታደርጊውም ልክ ከውሃ ውስጥ ካወጣሽው በኋላ ቢሆን ጥሩ ነው።
4. ጥፍሮችሽን መሞረድና በቅርፅ መቁረጥ፦ የጥፍርሽን አካል በሞረድ መሞረድና ስትቆርጪ ደግሞ መሀል ላይ ቀጥ አድርገሽ ዳርና ዳር ላይ በክብ ቅርፅ አድርጊ።
5. ማር መቀባት፦ በትንሹ ማር መቀባት ወደ እግርሽ የሚመጣውን ደም በመጨመር ውበት ከማጉላቱም በላይ የቆዳ ቀዳዶችን በመክፈት ጥሩ ስሜት ይሰጥሻል።
6. ሎሽንና ማሳጅ፦ ሎሽኑ የእግርሽን እርጥበት ስለሚጠብቁ በቀስታ ማሳጅ እያደረግሽ ቀቢ።
7. ካልሲ ማድረግ፦ በመጨረሻም ካልሲ በማድረግሽ ሎሽኑ በደንብ ወደ ቆዳሽ ውስጥ እንዲሰርግ ያደርጋል።
Comments
Post a Comment