ጣይቱ ብጡል ፤ የአቻ ጋብቻ ቀማሪ
የጣይቱ ብጡል የፍቅር ሕይወት
ጣይቱ ብጡል የሰለሞን የዘር ግንድ ካላቸው ራስ ብጡል ሐይለማርያም፣ ቤተሰባቸው አብዛኛውን የሰሜን ኢትዬጵያ ይመራ የነበረ፣ በወሎ ነው የተወለዱት። ቤተሰቧ የክርስቲያንና ሙስሊም ቅልቅል ሲሆን ሶስተኛ ልጅም ነበረች።ጣይቱ እንደአብዛኛው ኢትዬጵያዊ እንስት ብልህ ነበረች። በዘመኑም ደግሞ ከአብዛኛው እንስት ኢትዬጵያዊ በላይ በደምብ ስለተማረች ግዕዝ ታነብና ትፅፍ ነበረ፣ ግጥም ትፅፍ ነበረ፣ በገና መጫወት ትሞክር ነበረ፣ እንደውም ቼዝ ሀሉ ትጫወት ነበረ የሚል ፅሑፍም አንብቢያለው።
ጣይቱ ትዳሮቿ በሙሉ ፖለቲካዊ አቅም ስለሚጨምሩ አምስት ጊዜ አግብታለች። እስኪ ባጭሩ እንቃኛቸው፦
1. የቴዎድሮስ ወታደር ለነበረ ሰው በ 10 ዓመቷ ተዳረች። ነገር ግን ባሏ በቴዎድሮስ በመታሰሩ ትዳሯ ብዙም አልዘለቀም።
2. ቀኝ አዝማች ዝቅአርጋቸው( የአፄ ምንሊክ ወንድም)፦ በጣም ጭቆና የበዛበትን ትዳር ያሳለፈችበት ሲሆን አንድ ቀን እናቴን ልጠይቅ ነው ብላ ከወጣች በኋላ ምንም ካሳ ምናምን ሳትጠይቅ በዛው ቀርታለች።
3. ያልተሳኩ ሁለት ጋብቻዎች፦ ጣይቱ ወደ የጁ ተመልሳ ሁለት ጋብቻ ከፈፀመች በኋላ እጅግ ኃብታም ሆና ነበረ። ነገር ግን በሁለተኛ ጋብቻዋ ግዜ የምታውቀው የየዛኔው ሳህለ ማርያም በነገሰ ግዜ ልቧ ሸፈተ።
4. አፄ ምኒሊክ ፪(ሳህለ ማርያም)፦ አፄ ምኒሊክ ሁለተኛ ትዳራቸው በፍቺ ከተጠናቀቀ በኋላ ይቀርቡላቸው የነበሩትን ወጣትና ቆንጆ ሴቶች ሀሉ እሺ ሳይሉ የ 43 ዓመቷን ጣይቱ ብጡል አገቡ።
Comments
Post a Comment