የሰልፊ ቅጣት
ሰልፊ( ራስን በፎቶ ማንሳት) ሲቀጣ
ሰልፊ ማለት ስመርት ስልክ ወይም የላኘቶኘ ካሜራ ተጠቅሞ እራስን ፎቶ ማንሳት ከዛም በሶሻል ሚዲያ ማጋራት ነው። በተለይ ከ16 ዓመት በፊት ሶኒ ሰልክ በፊት ለፊት በኩል ካሜራ ይዞ ከመጣ በኋላ እንዲሁም ከ ስምንት ዓመት በፊት ኢንስታግራም በራሱ ፎቶ ማሳመር የሚችል ቴክሎኖጂ ካመጣ በኋላ በመላው ዓለም በጣም ታዋቂና ተወዳጅ ድርጊት ሆኗል።
መቼም ፌስ ቡክ ገፃቹን ስትከፍቱ በጣም ቢያንስ አንድ ሰው ሰልፊ አንስቶ ገፁ ላይ አድርጎ ማየታቹ አይቀርም። በቀን በአማካይ 715ሚሊየን ሰው የሚጎበኘው ፌስ ቡክ ላይ ምን ያህል ሰው ዛሬ ሰልፊ እንደለጠፈ አስቡት። ከነዚህ ሁሉ ሰልፊዎች ደግሞ ተለይቶ ለመታየት የማይደረግ ጥረት የለም። በዚህ ጥረት ውስጥ ነው እንግዲህ ሰልፊ ማንሳት ሊቀጣ የሚችለው። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የማያዳግም ቅጣት። እስኪ የማያዳግም ቅጣት የተቀጡ አምስት ሰዎችን እንይ።
ሰልፊ ለማንሳት ሲሉ ህይወታቸውን ያጡ አምስት ሰዎች፦
1. በድብ ህይወቱን ያጣ፦
በህንድ፣ ኦዲሻ ከተማ ኘራቡ ባታራ የተባለ ግለሰብ ከሰርግ ሲመለስ ካጋጠመው የቆሰለ ድብ ጋር ሰልፊ ሲያነሳ አብረውት የነበሩ ጓደኞቹ ተው ይቅርብህ እያሉትም ቢሆን ወደ ድቡ በጣም በመጠጋቱ አደገኛው ድብ እዛው ይዞት ነፍሱ ወታለች። የጓደኞቹ ድቡን የማስጣል ጥረት የተሳካውም ከዛ በኋላ ነው።
2. በሽጉጥ ጭንቅላቱን ያፈነዳ፦
በዋሽንግተን ዲሲ አንድ ሰው ከፍቅረኛው ጋር እየተፈራረቁ ሰልፊ ያነሳሉ። ያው ብዙ ሰው እንዲያይላቸውም የሱን ሽጉጥ አንዴ ግንባራቸው ላይ አንዴ አፋቸው ውስጥ አንዴ ጉንጫቸው ላይ እያደረጉ ይነሳሉ። በአንዷ ቅፅበት ግን እሱ ግንባሩ ላይ አድርጌ እነሳለው ካለ በኋላ ሽጉጡን ግንባሩ ላይ አድርጎ ባዶ የመሰለውን ሽጉጥ ቃታ ሳበ። ሽጉጡ ጥይት ነበረው።
3. ሃምሳ ሜትር ገደል ውስጥ የወደቀው፦
በቻይና ሃገር ዢህጃንግ ስፍራ የሚገኘውን የውሃ ፏፏቴ ይጎበኝ የነበረ ሚስተር ቼን የተባለ ቻይናዊ በሰልፊ ስቲክ(ካሜራ ማርዘሚያ ዘንግ) እራሱን ለማንሳት ሲጥር በድንገት መሬት ከድቶት ወደ ፏፏቴው ገደል ወድቆ ህይወቱን አቷል።
4. ከድልድይ ወደቀች፦
ፖላንዳዊቷ ሲልወያ ራችሄል የህክምና ተማሪ ነበረች። ስፔን ለጉብኝት ሄዳ ፑንት ደ ትሪያና የሚባል ድልድይ ላይ ሰልፊ ስታነሳ እግሯ ይከዳትና ከድልድዩ ትወድቃለች ወዲያው ህይወቷ አልፏል።
5. አውሮኘላን የከሰከሰው ሰልፊ፦
የሃያ ዘጠኝ አመቱ ሴሳ በአሜሪካ የኮሎራዶ ነዋሪ ሲሆን አብሮት ከነበረው ተጓዥ ጋር ሰልፊ እያነሱ ወደ ሶሻል ሚዲያ ሲልኩ አውሮኘላኗ እጅግ ወደ መሬት መቅረቧን አላስተዋሉም ነበረ። በአውሮኘላኑ ላይ የተገጠመው ካሜራ እንዳሳየው አውሮኘላኑ ሲከሰከስ ሁለቱም ማለትም ፖይለቱና ተጓዡ ስልካቸው ላይ አተኩረው ይፅፉ ነበረ።
Comments
Post a Comment