ይልኙታ ወይስ ፍራቻ?


ይሉኝታ፤ ለያዘን
ይሉኝታ በሃገራችን ዜጎች አስተሳሰብ ውስጥ ለዘመናት የኖረ፣ የራሱ የሆነ ጥቅምም ጉዳትም ያለው ባህሪ ነው። ዛሬ ማወራው ግን ስለሚያሳጣን ነገር ነው። ይሉኝታ ማለት በእኔ አመለካከት የራሳችንን ምቾትና ስሜት ለሰዎች ምቾትና ስሜት ስንል መሰዋት ማድረግ ነው። መስዋትነት ስንከፍል ደግሞ በምላሹ የተወሰነ ጥቅም ወይም እርካታ ማግኘት አለብን። የዛሬው ትኩረቴ ይሉኝታችን ከንቱ የሚሆንበትን ሁኔታ ማስረዳት ነው። ከንቱ ስል መስዋቱ ጉዳት እንጂ ጥቅም የሌለው ሲሆን ማለቴ ነው።

ማህሌት ክላስ ውስጥ እየተማረች እያለ አስተማሪው በሚያስረዳበት ሰዓት በእረፍት ሰዓቷ ጠጥታው የነበረው ለስልሳ መጠጥ ሽንቷ እንዲመጣ አድርጓል። መጀመሪያ ላይ ያሰበችው እስከ ክላሱ መጨረሻ እታገሰዋለው ነው። ነገር ግን ሦስት ደቂቃ እንኳን ሳይሞላ በጣም ያስጨንቃት ጀመረ። ሽንቷን የወጠራትን ያህል ያስጨነካት ደግሞ አስፈቅዶ የመውጣቱ ይሉኝታ ነው። ፍራቻ አይደለም ይሄ ይሉኝታ እንጂ። ማሂ ታዲያ ሽንቷ ከመጣባት ጊዜ ጀምሮ አዕምሮዋን ያዘው የሰውነቷ ጥያቄና የያዛት ይሉኝታ ነው። አምስት ደቂቃ ለማይወስድ መፍትሔ ሁለት ነገር ማሂ ተከስቶባታል ኩላሊቷን በማስጨነቋ የጤና ችግር እና አዕምሮዋን በማስጨነቋ ትምህርቱ።

የሆነ ቀን በታክሲ እየሄድኩኝ ያጋጠመኝን ልንገራቹ። ሰዓቱ ታክሲ የሚጠፋበት ስላልሆነ አልሞላም እና አንድ ወጣት ልጅ እኔ ከተቀመጥኩበት መቀመጫ ፊት ያለው መቀመጫ ላይ ተቀመጠ። ነገር ግን መቀመጫው መደገፊያ የለውም ነበረ። ይህንን አይቶ ወዲያው ቦታ ይቀይራል ስል ዝም ብሎ ቁጭ አለ። ያለመደገፊያ በመኪና መጓዝ በወገባችን እንደመቀመጥ ይቆጠራል እጅግ ከባድ ለሆነ የጀርባ ህመም ይዳርጋል። ገና ከመኪናው ሳይወርድ ሁሉ ሊሰማው ይችላል። ከጎኑ ወዳለው መቀመጫ ለመቀየር ይሉኝታ ስለያዘው እስክወርድ ድረስ የፊቱን ጭንቀት እያየው ነበረ። ወደ ጎንህ ወንበር ቀይር እንዳልለው ይሉኝታ ያዘኝ።

በትምህርትም፣ በህይወትም ጎበዝ የሆነ ሰው ታውቃላቹ? ቤዛ እንደዛ ናት። በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ ተመርቃ ስራ ለመቀጠር የፅሑፍ ፈተናውን ካለፋት ጥቂት ሰዎች አንዷ ናት። የቃለመጠይቁንም ፈተና በሚገርም ሁኔታ አልፋዋለች። ቀጣሪዎቹም ላስቸኳይ ክፍት የስራ ቦታ እሷን ስላገኙ ተደስተዋል። ከቀናት በኋላ ስራ እንድትጀምር ሲደውሉላት ስልኳ አይሰራም ለካ ስልኳ በሌላ ሰው የወጣ ኖሮ ቶሎ ማስከፈት አልቻለችም። በኋላ ቀጣሪዎቹ ሁለተኛውን ልጅ ቀጠሩ። የተሻለ ክፍት የስራ ቦታ እዛው መስሪያ ቤት ሲወጣ ለማመልከት ይሉኝታ ያዛት።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!