ቃል ዓለም ይፈጥራል፤ ሳይንቲስቶች


ዓለም የተፈጠረውም የሚፈጠረውም በድምፅ ነው

ከጥንት ጀምሮ ሲነገር የኖረውም ሆነ የዘመኑ ሳይንስ የሚስማማበት አንድ እውነት አለ ይህም ዓለም የተፈጠረው ከኅይለኛ የድምፅ እርግብግቢት መሆኑ። እንደሚታወቀው የጥንት ሰዎች ህመም ለማዳን፣ የማይታየውን ዓለም ለማየት ወይም ደግሞ የመጠቀ አእምሮ ለማግኘት ብርሃንን፣ ድምፅን፣ ቀለማትን የመሳሰሉትን ይጠቀሙ ነበር።

በተለይም የጥንት ሰዎች በመነባነብና በከበሮ በመታገስ ያመልኩና ይደሰቱም ነበር። በኋላም በጣልያን ኀገር ስድስት የተለያዩ የድምፅ እርግብግቢቶች በኋላም ሰባተኛ ተጨምሮ ሶልፌጂዮ ስኬል ተብሎ ተስተካክሎ ተዋወቀ። የምንሰማው ሙዚቃም ይሁን ደምፅ በነዚህ እርግብግቢቶች ሲሰናዳ ልክ የድሮ ሰዎችን ለፈውስ፣ ለመዝናናት ይጠቅም እንደነበረው አሁንም ይሰራል ማለት ነው።
የሰውነታችን 70% ውሃ እንደሆነ ይታወቃል። በተለያየ የድምፅ አይነት ውሃ ምን ያህል እንደሚቀየር ሙከራ የሰሩ ሳይንቲስቶች እነዚህን ፎቶዎች አንስተዋል። ፎቶዎቹ የሚያሳዩት አንድ አይነት ድምፅ እየተሰጣቸው እንዲቀዘቅዙ የተደረጉ የውሃ ብናኝ በረዶዎችን ነው።

በተጨማሪም ድምፅ ቅርፆችን ይሰራል። የሚቀጥለው ፎቶ የሚያሳየውም ይህንን ነው። ሳይንቲስቶች የደቀቀ የጨው ዱቄት ከትልቅ ስፒከር በላይ በተቀመጠ ጥቁር ጨርቅ ላይ በተኑ። ከዛም በኋላ ድምፅ ከስፒከሩ ሲወጣ የጨው ዱቄቱ መርገብገቡ አይገርምም ነገር ግን የዘፈቀደ እንቅስቃሴ አይደለም ጨው ዱቄቱ ያደረገው፤ የተለያየ ድምፅ ሲወጣ የተለያየ ውስብስብ ነገር ግን የፀና ቅርፅ ሰጠ። አንድ ድምፅ ሲወጣ በአንድ አይነት ድምፁ ሲቀየር በሌላ አይነት እየሆነ አስገራሚ ቅርፆች ይሰጣል።

ስለዚህ የድምፅ አቅምና ኀይል በደንብ ተጠንቷል ብላቹ ታስባላቹ። የነገው ዓለማችን በድምፅይ የተመሠረተ ይሆን ይሆናል።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!