ፍቅር ሲይዝ፤ ህግ አይሰራም


ሲወዱ፤ ህግ አይሰራም
በተፈጥሮዬ የራሴን ነገር በራሴ ብቻ ማድረግ የምወድ ወንዶች ቢቀርቡኝ እንኳን ለጓደኛነት ወይም ለታናሽ እህትነት ብቻ እንዲሆን የምፈልግ ትኩረቴ ትምህርትላይና አንድ አንድ ግዜ ለምጫወተው ቅርጫት ኳስ መለማመድ ነበረ። በዮኒቨርስቲ ውስጥ ምንም ወንድ ጓደኛ ማለቴ እንደፍቅረኛ እንደማይኖረኝ የወሰንኩት ባለፈው ዓመት ሰርቷል ዘንድሮም ይኸው አንድ ሴሚስተር ልጨርስ በሆነበት ጊዜ ማለትም ከአንድ ወር በፊት የሆነውን ነው የምነግራቹ።
ስሜ ሔርሜላ ይባላል የሳይኮሎጂ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ስሆን ጎበዝ ከሚባሉት ተማሪዎች አንዷ እንደሆንኩ በውጤቴ አውቀዋለው። ብዙ ግዜ ማጥናት የምወደው በምሽት ሲሆን በተለይ ፈተና ሲቀርብ ወደ ካፌ ፌርሙሴን ይዤ ሄጄ ሻይና ቡና ሞልቼበት በጊዜ አልጋዬ ላይ ወጥቼ ሊነጋ ሲል ነው ትንሽ ምተኛው።

የዛሬ ወር ላይ የክላሴ ተማሪ ልጅ ፣ ደስ የሚለኝ ልጅ ነው፣ ልክ ፌርሙሴን ይዤ ከካፌው ስወጣ በር ላይ አገኘኝና ስለፈተና ኘሮግራም ከጠየቀኝ በኋላ፣
‘ዛሬ ደግሞ አምሮብሻል፣ ይሄን ሴሚስተርማ ወንድ ሳትስሚ እንዳያልፍ’
ካለኝ በኋላ እየሳቀ ወደ ካፌው ገባ ባቆምኩበት እንዴ ከምር ግን አበዛውት የሚል ኀሳብ መጣብኝ ዞር ብዬ መግባቱን ሳይ እንደማኩረፍ ብዬ ወደ ዶርሜ እየሄድኩ ‘ትንሽ ቢያዋራኝ ኖሮ’ አልኩኝ በሆዴ።
ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ በቃ የብቸኝነት ውሳኔዬ አፈር በላው። ሳሚ ያቺን ቀልድ ከቀለደ ጀምሮ አዕምሮዬን ተቆጣጠረው። ክላስ ውስጥ ከወደፊት መቀመጤን አቁሜ በየመሃሉ ሳምሶን እንዲታየኝ መጨረሻ መቀመጥ ጀመርኩኝ። ሲፅፍ ደስ ሲል፣ ቀና ብሎ የአስተማሪውን እንቅስቃሴ ሲከታተል ደስ ሲል፣ ከክላስ ሲወጣ አካሄዱ ደስ ሲል፣ በቃ ምን አለፋችሁ ተለከፍኩኝ።
ሳሚ ረዘም ያለ፣ የቀይ ዳማ፣ ጓደኞቹ ሁሉ እጅግ የሚወዱት ከክላሳችን ሴቶችማ የማትመኘው የለችም እኔም ብዙ ስለሱ ሰማ ነበረ ባልሰማ አልፈው ነበረ እንጂ። እንደውም አንዷ ጓደኛዬ ማታ ማታ ተሰብስበው ማለትም ሳሚንም ጨምሮ ማጥናት እንደጀመሩና እኔም አብሬያቸው እንድሆን እንደሚፈልጉ እንደውም ኀሳቡን ያመጣው ሳሚ እንደሆነ ነግራኝ ነበረ። ባልሰማ አለፍኳት እንጂ።

ከንድ ሳምንት በኋላ ለምህረት፣
‘ዛሬ የት ነው ምታጠኚው’ አልኳት እያወኩት መልሱን
‘ከነሳሚ ጋር ነዋ፣ ምነወ?’ አለቺኝ ጥያቄው ገርሟት ነው መሰለኝ
‘እኔ ምንም ሙዴ እየመጣ አይደለም ዶርም፣ ልምጣንዴ እናንተ ጋር ዛሬ’
‘አንዴ ሔርሚ፣ አግኝተነው በኋላ ግን ኀሳብሽን እንዳትቀይሪ’
‘ኖ ዌይ’ አልኳት ለምን እንደዛ እንዳልኩ ትንሽ እንኳን ባለመጠርጠሯ ደስ ብሎኝ

ያቺ ቀን እንዴት ትምሽ፣ ክላስም እሁድ ስለነበረ የለም በቃ ቀኑን ሙሉ ኀሳቤ ሳሚ ሆኖ ዋለ። በጊዜ እንገናኝ ተባብለው ነበረ አስራ አንድ ሰዓት ላይ አንድ ባዶ ክፍል አግኝተን ምህረት ለሳሚ ደወለችለት። ከአምስት ደቂቃ በኋላ ከአንድ ጓደኛው ጋር መጡ። ሰዓቱ የማይሆን ሰዓት እንደሆነና እራት በልተን አንደኛችንን ብንጀምር ይሻላል ሌሎች ልጆችም አንደዛ እንዳሉ ሳሚ ሲናገር ደስ አለኝ ‘ከሱ ጋር ለማውራት ነው የመጣሁት’ አልኩኝ በሆዴ። ከዛም የት እንደምንበላ ተነጋግረን እነ ምህረት ከፊት እኔና ሳሚ ከኋላ መጓዝ ጀመርን። ያወራነው ሁሉ ልቤን ይነካው ነበረ ልክ የምንበላበት ቤት ጋር ስንደርስ፣
‘ስልክሽ እኮ የለኝም ግን’ አለኝ በሚያምሩት ጥርሶቹ ፈገግ እያለ
’09……’ ብዬ ከአንድ አንድ ነው የሰጠውት
ከዛማ በቃ በቴሌግራም ሆነ ንግግራችን። የማናወራው ነገር የለም። ማታ ከግሩፑ ጋር አጥንተን ለእረፍት ብለን ወተን ከሁለት ሰዓት በኋላ እንመለሳለን አንድአንዴም በዛው ወደዶርም እኔዳለን ሊነጋ ሲል ማለት ነው። ምህረትም፣
‘እናንተ ግን እያበዛቹት ነው’ ትላለች የወሰድኩትን ደብተር ምናምን እየሰጠችኝ ሀሌም እንዲ ብላ ነው ምትሰጠኝ
እኔና ሳሚ የማናወራው ነገር የለም። እጅግ ደስ ይለኛል የልቤን ስነግረው። እሱም እንደዛው እንደሚሰማው ያስታውቃል። ነገር ግን ለመጀመሪያ ግዜ የተሳሳምነው ትላንትና ነው።

ታሪኩን እንደነገረቺኝ አቅርብዋለው።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!