ሁለተኛ ' ደህና ነኝ' አልልም
ሰዎች እንዴት ነህ ሲሉኝ ‘ ደህና ነኝ’ ማለት ያቆምኩበት ምክንያት
የዛሬ ሶስት ዓመት ገደማ በጣም የምወዳት እናቴን በሞት ተለየኋት። አጠገቤ የነበሩት ቤተሰቦቼ በሙሉ አዝነውም ስለነበረ እራሳቸውን እያፅናኑ ነው በቅርቤ የነበሩት ጓደኞቼና የማውቃቸው ሰዎችም እንዴት ነህ አሁን ባሉኝ ቁጥር መልሴ ‘ ደህና ነኝ’ የሚል ነበረ።
በዚህም ምክንያት ጠያቂዎቼ መርዳት እየቻሉ ደህና ስለምመስላቸው ትተውኝ ነበር። ነገር ግን የሚወደውን ሰው ያጣ ሁሉ እንደሚያውቀው ሃዘኑ ሁሌም ይኖራል። ስለዚህ አሁንም እናቴ ትዝ ብላኝ ስተክዝ የሚያዩኝ ጓደኞቼ ምነው ደህና አይደለህም እንዴ? ሲሉኝ ‘ ደህና ነኝ’ ነው መልሴ።
በቅርቡ ግን ባገኘሁት የስነልቦና ምክር ስጠየቅ ዝም ብዬ ደህና ነኝ ላለማለት ከመወሰኔም በላይ በኀዘን የተያዙ ወጣቶችን የሚያወያይ ድርጅት አቋቁሜያለው። በውስጡ ወጣቶቹ ደህና ነኝ የሚለውን መልስ ትተው ስለኀዘናቸው ስለሚሰማቸው ስሜት የመሳሰሉት ይወያያሉ።
ለህብረተሰቡም የማስተላልፈው መልክት አለ ይላል የ 25 ዓመቱ እንግሊዛዊ ጄምስ፤ ሰዎች የሚያዝን ሰው ደህና ነኝ ቢልም ለይሉኝታ እንደሆነ በመረዳት ቀርበው ሊያፅናኑ ይገባል። በኀዘን ውስጥ የሚገኝ ሰው የስነልቦና ድጋፍ ያስፈልገዋል፣ ውስጡን ማድመጥ ኀዘኑን መጋራት አስፈላጊ ነው ብሏል።



Comments
Post a Comment