በጥዋት መነሳት፤ በብልኀት


በጥዋት መነሳት፤ በብልሃት
እንዴት እንደሚያናድ መቼም የምታውቁ ታውቁታላቹ። ምርታማና ጥሩ ቀን ለማሳለፍ በጠዋት መነሳት ወሳኝ መሆኑን እያወቃችሁ ግን ሁልጊዜ ጥዋት ቶሎ መንቃት ሞት ይሆንባችዋል። ስለዚህ የሰዓት አላርም ብትሞሉም ለ 5 ደቂቃ ስኑዝ(እንዲታገስ) ከዛም ድጋሚ ስኑዝ ከዛም ድጋሚ ስኑዝ…….. ለምታደርጉ እነዚህን መፍትሔዎች ሞክሩ እስኪ።

1.በየቀኑ አንድ ደቂቃ እየቀነሳቹ አላርም ሙሉ፦
በተለይ ከላይ እንዳልኩት ስኑዝ የምታረጉ ካላቹ ሰውነታችሁ ለመንቃት ሰዓት ይፈልጋል ማለት ነው። ስለዚህ ምንም ሳይታወቃችሁ በጠዋት ከሚነሱ ስኬታማ ሰዎች ጋር ለመቀላቀል እንዲህ አድርጉ፦
• በጥዋት11:45 ለመነሳት ከፈለጋቹና ከ12:30 ንቅንቅ ማለት ከከበዳቹ እንዲህ አድርጉ፤ በየቀኑ አንድ ደቂቃ እየቀነሳቹ አላርም ሙሉ። ለምሳሌ 12:30 የነበረውን አላርም ነገ 12:29 ከነገ ወዲያ 12:28 ቀጥሎ 12:27 እያላቹ በአንድ ወር ውስጥ ሰውነታችሁም ሳይጨናነቅ በ11:45 መንቃት ይለምዳል።
2. በትንሽ ስኬት ጀምሩ፦
አንድ ታዋቂ የገንዘብ አጠቃቀም ምሁር እንዳለው ‘እዳ መክፈል መጀመር ያለባችው ከትንሽ እዳ ነው እሱም ትልቅ እዳቹን መክፈል እንደምትችሉ ጭንቅላታቹን ያምናል ከዛም ታደርጉታላችሁ ‘ ብሎ እንደመከረው ነው።
• ለምሳሌ 11:45 ጥዋት ለመነሳት ወስናችኋል እንበል፣ እስከዛሬ ምትነሱት ግን ጥዋት2:30 ከሆነ 11:45 በጣም እሩቅ ሆኖ ስለሚሰማችሁ። መጀመሪያ 15 ደቂቃ በመቀነስ በርሱ መንቃት ልመዱ ከሳምንት በኋላ 30ደቂቃ ቀድማችሁ መንቃት ተለማመዱ። ከአንድ ሳምንት በኋላ 45 ደቂቃ ቀድማችሁ መንቃት ተለማመዱ። ከሳምንት በኋላ 45 ደቂቃ ቀንሱና በሚቀጥለው ሳምንት 30ደቂቃ ብቻ በመቀነስ ግባችሁን ታሳካላችሁ።

 3. በጥዋት መነሳት ከሚሳካላቸው ሰዎች ጋር ቀጠሮ መያዝ
ይህ የሚረዳን በሦስት መንገድ ነው።
 • ቀጠሮ ማክበር ስላለባችሁ ኅላፊነቱ
 • ሰውነታችሁ እራሱ ኅላፊነት እንዳለባቹ ስታስቡ የመንቃት ባህሪ ስላለው
• በተለይ የምታጡት ነገር ካለ በሰዓቷ መንቃታቹ ስለማይቀር 4. ለጥዋት አካባቢያችሁን ማሰናዳት፦
• የአላርሙን ቦታ አርቃችሁ ማስቀመጥ
 • የሻይ ማፍያ ወይም ጥዋት ሚጠቅማችሁን ነገር ሁሉ ፊት ለፊት ማድረግ
• ልብሳችሁን አዘጋጅታችሁ በቅርባችሁ ማድረግ


 5. በጥዋት ለመነሳት የሚያስገድዳችሁን የምትወዱትን ነገር መከወኛ ሰዓት ጨምሩበት
 • ለምሳሌ ጥዋት 30 ደቂቃ ጨምራችሁ የምትነሱት ሩጫ ለመሮጥ ከሆነና ሩጫው የሚያስጠላችሁ ከሆነ ጥዋት መነሳትን ከሩጫው ጋር ስለሚያያዝባችሁ ለመነሳት ይከብዳችዋል። ስለዚህ የምትወዱትን ለማድረግ ተጨማሪ የጥዋት ሰዓት ያዙ ለምሳሌ ዳንስ የምትወዱ ከሆነ የኤሮቢክስ ቪዲዬ እያያችሁ ለመደነስ ምትነሱ ከሆነ ከስፖርቱም አይቀርባችሁም ማለት ነው።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!