የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ወይስ የመጨረሻ ልጅ መሆን ይሻላል?
የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ወይስ የመጨረሻ ልጅ የሚሻለው?
የመጀመሪያ ልጅ፣ የመጨረሻ ልጅ፣ ሁለተኛ ልጅ፣ ወይም ብቸኛ ልጅ መሆናችሁ ወደዳችሁም ጠላቹ ማንነታቹን ወይም ያላችሁን ባህሪ ይወስናል። ዶ/ር ኬቭን ሌማን ላለፉት አርባ ዓመታት የቤተሰብ ልጆችን የትውልድ ቅደም ተከተልና ባህሪ አጥንቷል። አንደሱ አባባል በምንም መልኩ የመጀመሪያ ልጅና ተከታይ ልጅ ተመሳሳይ ባህሪ አይኖራቸውም። እስኪ ለምሳሌ አንድ የማውቀው ቤተሰብ ውስጥ ሁለተኛው ልጅ እጅግ የታወቀ ቀልደኛና ተዋናይ ሲሆን የመጀመሪያው ደግሞ እጅግ የተከበረ የፖለቲካ አዋቂና ተመራማሪ ነው ነገር ግን ሁለቱም ከአንድ ማህፀን የወጡ ናቸው።
ለሃያ ዓመት የቤተሰብ አማካሪ የሆነችው ሜሪ ዋላስ ደግሞ የሚከተለው ቀመር ይሰራል ትላለች፦
የትውልድ ቅደም ተከተል + አስተዳደግ = ባህሪ
ለምሳሌ የመጀመሪያ ልጅ የወለዱ ሰዎች ልጁ እንደ መሞከሪያ ነው፤ ሙከራውም በተፈጥሮ ከሚያውቁት ጋር በሂደት እየተማሩ የሚሄዱበት ነው ለወላጆች። ይህ ደግሞ ልጁን በባህሪው እንከን የሌለበት ለመሆን ከሚገባው በላይ የሚጥርና ሁሌም ወላጆቹን በማስደሰት ብቻ የሚኖር ሊያደርገው ይችላል። ሁለተኛ ልጅ ሲወልዱ ወላጆች ትንሽም ልምድ ስለሚኖራቸውና እንዲሁም ሌላ ልጅ ስላለ ለሁለተኛው ልጅ ከመጀመሪያው እኩል አያዩትም ይህ ደግሞ ሁለተኛው ልጅ እንደመጀመሪያው የበዛ ጥንቁቅ እንዳይሆን ሊያደርገው ይችላል።
የመጀመሪያ ልጅ ባህሪያት፦
• አስተማማኝ ወይም ታማኝ ናቸው
• ተጠራጣሪ ናቸው
• ሥርዓት በእጅጉ ይጠብቃሉ
• ጠንቃቃ ናቸው
• ተቆጣጣሪ ናቸው
• ስኬት ላይ ያተኮሩ ናቸው
የሁለተኛ ልጅ ባህሪያት፦
• ለሰው ደስታ ቅድሚያ ይሰጣሉ
• አመፀኛ ናቸው
• ለጓደኝነት ትልቅ ቦታ አላቸው
• ብዙ ሰው ያውቃሉ
• ሰላም ፈጣሪ ናቸው
የመጨረሻ ልጅ ባህሪያት፦
የመጨረሻ ልጅ ብዙ ግዜ ነፃነት ይሰጠዋል ምክንያቱም ወላጆች የልጅ ማሳደግን በመጀመሪያው፣ በሁለተኛው፣ ምናልባትም በሦስትና አራተኛው ስለተለማመዱ ሊሆን ይችላል።
• ጨዋታ ወዳድ
• ነገሮችን ቀለል አርገው የሚያዩ
• ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ
• ወጣ ወጣ የሚያበዙ
• ትኩረት ሁልጊዜ የሚሹ ናቸው
ከላይ የተቀሱት ባህሪያት ባብዛኛው ይታያሉ ነው እንጂ ሁሌም ልክ ነው ማለት እንዳልሆነ ግን ሊሰመርበት ይገባል።
Comments
Post a Comment