ያገሬ ሹፌሮች ኮራውባቹ


ሹፌሮች ኮራንባችሁ
መቼም የመኪና አደጋው ብዙ መሆኑ የማይካድ ሀቅ ቢሆንም እንደዚህ አይነት ዜና ስንሰማ ደሞ በወገኖቼ ኮራለው። ኢትዬጵያ ውስጥ መንዳት እጅግ ፈታኝ ከመሆኑ የተነሳ እስኪ ከውጪ የመጣ ዘመዳቹን እዚህ መንዳት ትፈልጋለህ ወይ ብትሉት በጭራሽ እንደሚል አልጠራጠርም። 

ለገና ዕረፍት ከአውሮፖ የመጣ ዘመዴ ሲነግረኝ’ በጣም ጎበዝ ሹፌር ስለሆንኩኝ መኪናዬ 2,400 ሲሲ ሆና ቱርቦ ናት’ አለኝ።

 2,400ሲሲ ጉልበት ያላው መኪና ማለት እንደ ከፍ ያለው ሃይሉክስ ሲሆን ቱርቦው ደግሞ ተጨማሪ ኅይል ይሰጠዋል። ይህም ማለት እጅግ እየፈጠነ መሄድ ይችላል ማለት ነው። እናም ዘመዴ ምን አለኝ
 ‘ ብዙ ግዜ እዛ ስነዳ የሚቀድመኝም የለም ጎበዝ እንደሆንኩና አብረውኝ የሚጓዙትን ሰዎችም ምቾት እንደማልነሳ ተመስክሮልኛል’ አለኝ። ‘ቢሆንም ግን የዚህ አገር ሹፌሮች ንቁና ቀልጣፋ ናቸው። ለምሳሌ መዞሪያ ላይ ከዋናው መንገድ የሚመጣው መኪና ሌላ መኪና ሊዞር ፍሬቻ እያበራ ቆሞ ካየ መዘጋጀቱ አይቀርም ድንገት ከዞረ ብሎ እናም ከዞረ በፍጥነት ያቆመዋል’ አለኝ። 
እኔም ገርሞኝ ‘እና ታድያ ይጋጭ እንዴ’ አልኩት። 
‘ እሱን እኮ ነው የምልህ በንቃት ይጠብቃል ቅድሚያው የራሱም ቢሆን እንኳን እዛ ቅድሚያው የኔ ከሆነ ቢዞር ባይዞር ሳልል እግሬን እንኳን ከነዳጅ መስጫው ሳላወርድ ነው ምነዳው’ አለኝ። 
‘እንዴ ቢዞርስ’ አልኩት አይኔን ከፈት አድርጌ እያየውት። 
‘በቃ እናልቃለና ግን አስታውስ ጎበዝ ሹፌርነቴ ተመስክሯል እዛ’ አለኝ። 
በጣም ገርሞኝ እየሳኩ ‘ እኔ ደግሞ በዚህ በማይመች መንገድ፣ በየቀኑ ለማጅ ሹፌር በማይጠፋበት መንገድ፣ አብዛኛው እግረኛ ከመኪና ጋር በሚጓዝበት መንገድ…….ኧረ ስንቱ በሹፍርና በየቀኑ የሚተዳደር ለዛውም የከፋ አደጋ ሳያደርስ በጣም በጣም ጎበዝ ናቸው እንጂ’ አለኝ።
ለማንኛውም ሹፌሮቻችን ውጪም እየተፈለጋቹ ስለሆነ አስኪ አጣሩ ለማለት ነው።


Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!