ባልሽን እንዴት ተዋወቅሽው?


10 ደስ የሚሉ የመጀመሪያ ትውውቅ ታሪኮች


10. እኔ አሰተናጋጅ ነበርኩ አርሱ ደግሞ ደምበኛ፦
ሁለታችንም ከፍቅረኞቻችን ተለያይተን ብቻችንን ነበርን ከዛ ስናወራም ሁለታችንም ድመት እንወዳለን እያለ እያለ ተዋደድን በኋላም ተጋባን።
9. ኀይስኩል እየተማርን በኮሪደር ላይ ስጓዝ ያየሁት ዓይን አስደነገጠኝ ለመጀመሪያ ጊዜም የሰው ልጅ የነፍስ መስኮት ነው በሚባለው አይኑ የተማረኩለት ልጅ እውነት እንደሆነ ያሳየኝ ያሁኑ ባሌ ነው።
8. 15 ዓመቴ ነበር እና መክሰስ ልበላ የገባውበት ምግብ ቤት ያስተናገደኝ ልጅ ላይ አይኔ ተተክሎ ቀረ ፣ ለካ እሱም ተሰምቶት ነበረና ልክ ስወጣ መቶ 'ማታ ፊልም እንይ ሲለኝ' ሳላንገራግር እሺ አልኩት። የዛኑ ቀን ማታ ፊልሙን እያየን ለመጀመሪያ ግዜ በወንድ ተሳምኩ፣ ከዛም የኸው ተጋብተን ደስተኛ ኑሮ እኖራለን።
7. ሳላስበው ላሸነፍኩት የዳንስ ውድድር ለማጥናት በምመላለስበት ላይብረሪ ውስጥ የሚሰራው ልጅ ሳላስበው በፍቅር ጠምዶኛል።

6. ተለምኜ የሄድኩበት ግብዣ ላይ አንድ ልጅ ሲገባ ተመለከትኩ በቃ የኔ መሆን አለበት ብዬ ሽንት ቤት የሴቶች ስብሰባ ጠራውና የተሰማኝን ነገርኳቸው በኋላም ጓደኞቼ አስተዋወቁን ዛሬ ከተጋባን 5 ዓመቱ ነው።

5. የሁለታችንም ጓደኛ በሆነ ሰው ሁል ጊዜ እንገናኝ ነበር ቀስ በቀሰም ብቻችንን መሆን ጀመርን በኋላም የዛሬ 19 ዓመት ተጋባን።
4. ምንም ዓይነት የወንድ ጓደኛ ዓይደለም ስለመሞከርም አላስብም ያልኩት ልክ እንደ ተመረኩኝ ነበር።  የትወና ትምህርት ለመማር ወስኜ ስለነበር ለመመዝገብ ወረፋ እስኪደርሰኝ ወጣ ብዬ ስልክ እያወራው ነበር አንድ በጣም የሚያምር ልጅ ባጠገቤ ያለፈው እንዳየሁትም ' ይህንማ አገባዋለው' አልኩኝ በሆዴ በጣም ነበር የገረመኝ እንደዛ ሲሰማኝ የሚገርመው ደግሞ አንድ ላይ መማር መጀመራችን በፍቅሩ እንዳልወድቅ የምክንያት መዓት እየደረደርኩኝ ነበር ሆኖም በመጨረሻ ተረታው።
3. ሰምንተኛ ክፍል እያለው በምናጠናበት ቦታ ላይ መቶ ሲተዋወቀኝ ቀልቤን ሳበው በኋላም በጣም ጣፋጭና ቅን ሰው ነበር። ኀይስኩልም እየተማርን አንዴ አበባ ይሰጠኛል አንዴ ግጥም ይፅፍልኛል ብቻ ብርም ስላልነበረው የረባ ነገር አርጎልኝ አያውቅም አንዴ ብቻ ቸኮሌት አንደሰጠኝ አስታውሳለው ቢሆንም ግን አፍቅሬው ነበር። የዛሬ አምስት አመት ተጋባን።
2. በጥዋቱ የፊዚክስ ላብራቶሪ ትምህርት ላይ የተዋወቀችውን የሚያምር ልጅ ጓደኛዬ ዶርሟ ቀጥራው ከጓደኛው ጋር እንደሚመጣ የነገረችኝ ቡናና ኩኪስ የዤላት እንድመጣ ስላሳሰበችኝ በቢጃማ ሆኜ ስደርስ ያለችኝ ልጅ ከነጓደኛው ቁጭ ብሏል። የልጁ ጓደኛ ነው ቀልቤን የሳበው። ይህ የሆነው ከ ሃያ አመት በፊት ነበር።
1. ሞዴሊንግ ለመስራት ለአንድ ሳምንት ግብዣ ተደርጎልኝ ያረፍኩበት ሆቴል ውስጥ የሚቀጥለው ክፍልን የያዘው ልጅ ከምገምተው በላይ ውብ ሆነብኝ። በተዋወቅን በ ሦስተኛው ቀን እዛው ተጋባን። ቤተሰቦቼ አብደሻል ሁሉ ብለውኝ ነበር እኔም ምንም ከማላቀው ሰው ጋር መጋባቴ ትንሽ አሳስቦኝ ነበር ነገር ግን ይኸው አሁን የሁለት ዓሠት ልጅ አለችን ደስተኛ ነን።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!