ቁጠባና ብድር የባንኮች ጨዋታ
በባንክ ምን ያህል ቆጠቡ? ምን አገኙ?
የባንኮች የኢንተረስት ሬት( ገንዘብ በመቀመጡ የሚኖረው ዋጋ ጭማሪ) በ ኢትዬጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው የሚወሰነው። ሳም ቲቪ ለመግዛት ከወሰነ በኋላ በየወሩ 1,000.00 ብር ባንክ ለማስቀመጥ ወስኖ ባንኩ የሚከፍለውን በየወሩ የሚታሰብ ኢንተረስትን ጨምሮ ከ ስድስት ወር በኋላ አንድም ወር ሳያዛንፍ ስላስቀመጠ ከ 6,000.00 ብር በላይ ስለሚያገኝ ደስ ብሎታል። ባንኩ ውስጥ ያገኘውን አካውንታንት ያለውን የገንዘብ መጠን እየጠየቀ ነው።
ዴቭ ለብድሩ የጓደኛውን ደሞዝ መተማመኛ አሲዞ ሳም በየወሩ ከሚያስቀምጥበት ባንክ 6,000.00 ብር ልክ ሳም የመጀመሪያ 1,000.00 ብሩን ሲያስገባ ወስዷል። 17% ኢንተረስት እንደሚታሰብበትና ከያዙት ወር ጀምሮ መመለስ ጀምሮ በስድስት ወር ውስጥ ለማጠናቀቅ ተስማምቷል።
እስኪ ለባንኩ እቺ ትንሽ ብር በ ስድስት ወር ውስጥ ምን እንደምትፈጥር እንይ። በኢትዬጵያ ብሔራዊ ባንክ አዋጅ ትንሹ በማስቀመጥ የሚገኝ ክፍያ 7% ነው ይላል። ሁሉም ባንክ እሷን ነው የሚያደርግ 8%, 9% ምናምን ማድረግ ቢችሉም ማለት ነው።
ሳም፦ 6ኛ ወር- 6,000.00 ብር + 123.70 ብር (የወለዱ ጠቅላላ ምጣኔ) = 6,123.70 ብር ያገኛል።
ዴቭ፦ 6ኛ ወር - በየወሩ 1,050.16 ብር እየከፈለ በስድስተኛው ወር ላይ 6,300.99 ብር ይከፍላል ማለት ነው። (300.99 ብር ወለድ)
ስለዚህ ባንኩ 300.99-123.70 = 177.29 ብር አገኘ ማለት ነው።
Comments
Post a Comment