የቪክቶሪያስ ሲክሬት የሜክአኘ ህግ
የቪክቶሪያስ ሲክሬት የሜክአኘ ህግ
ከቪክቶሪያስ ሲክሬት የምንማረው ሰባት የሜክአፕ ህጎች
በፈረንጆቹ ያለፈው አመት በሻንጋይ፣ ቻይና ትልቅ የፋሽን ትርኢት ተካሂዶ ነበር። ሞዴሎቹን በዋናነት ሲያስውብ የነበረው ደግሞ በዓለም ላይ አሉ ከተባሉት ሜክአኘ አርቲስቶች የሚመደበው ቶም ፒቹ ነበር። ፒቹ ‘ ሞድሎቹን ያሳመርኩት በተለይ ዓይናቸው ላይ አተኩሬ ፈታ ያለ መልክ እንዲኖራቸው ነው።’ ብሏል።
እስኪ ሞዴሎቹን እንዴት እንደሚያሳምርና ህጎቹን እንቃኝ፦
1. የቆዳ እንክብካቤ በጣም ጠቃሚ የመጀመሪያ ህግ፦
መጀመሪያ ከቂቤና ዘይት የተሰራ ቅባት በመጠቀም የሞዴሏን ፊት ቀባ። ‘ ይህ ሌሎች ሜክአፖች ከፊቷ ጋር እንዲዋሃድ ይረዳል።’ አለ። ከዛም ቅባቱን ፊቷ እንደተቀበለው አረጋግጦ በስሱ የፊት ጄል ቀባት።
2. ኮንሲለር የፊታቹን ገፅታ በሙሉ አይሸፍን፦
ኮንሲለር ማለት ፊታችን ላይ ሊኖሩ የሚችሉ የከለር ልዩነቶች እንዲያስተካክል የምንጠቀመው ሜክአኘ ሲሆን ብዙ ግዜ በተለይ ጠቆር ለሚለው የዓይን ስር ሳሳ ያለ ኮንሲለር ይጠቀማል ሰው። ፒቹ ግን የፊታችንን የከለር ልዩነት ብንጠብቅ የተሻለ ውበት ይኖረዋል ይለናል።
3. ፋውንዴሽንን በጣም በስሱ፦
እንደ ፒቹ አባባል ከቻላችሁ እንደውም ዝለሉት ይለናል። ፋውንዴሽን መጀመሪያ ላይ አምሮ ይታይና ከቆይታ በኋላ ውበቱ ይደበዝዛል። ስለዚህ ከተቀባችሁም በጣም በስሱ ይሁን ይላል።
4. ማስካራ መቀባት፦
ፒቹ የሞዴሏን ሽፋሽፍት ሁለቴ በማስካራ ቀባ። ከዛም የሞዴሏ ዓይን ተዓምራዊ ነገር ግን ተፈጥሯዊ መልክ ያዘ። ‘ ማስካራ ከሁሉ ነገር በፊት መቀባት አለበት ቶሎ ስለሚደርቅ አያስቸግርም’ ይላል ፒቹ።
5. የዓይን መስመር፦
‘ከፈለጋቹ እንደኔ የአይን ሽፋሽፍት ተከትላችሁ በነጥብ በነጥብ መስመር ከሰራቹ በኋላ በኩል ማስመር ትችላላችሁ እኔ የዓይን ኮክቴል እለዋለው’ አለ የሞዴሏን አይን እያሳመረ። ካልሆነ ግን በኩል ብቻ መስመርም ይቻላል ይለናል።
6. ደብዛዛ ግን ማራኪ፦
የታችኛውን የሽፋሽፍት መስመር ከሻዶው ከለር ጋር ማመሳሰል። ፒቹ የተጠቀመው ደብዘዝ ያለውን ቡናማ ከለር ኩል ሲሆን መስመሩም ሄዶ ከሻዶው ጋር ተመሳሰሏል።
7. ሊኘ ስቴይን መጠቀም፦
ሊኘ ስቴይን( ፈሳሹን የከንፈር ማስዋቢያ) የተጠቀመው ፒቹ ከቡናማው የዓይኗ ሻዶውና ሽፋሽፍት ጋር እንዲመስል ደብዛዛ ቀይ ነው። ‘ ሊኘ ስቴይን ከንፈራችን በደንብ ስለሚቀበለው ከላይ ያሀው ቢለቅ እንኳን ከለሩ ከከንፈራችን ቶሎ ስለማይጠፋ መርጠዋለው’ ብሏል።




Comments
Post a Comment