በሚስጥር በማፍቀሯ፣ ተሳሳተ ወንድሟ


አህቱ የተደፈረች የመሰለው ታዳጊ
በድንገት ወደ ቤት የመጣው ታዳጊ በመስኮት ያየውን ማመን ያቅተዋል የሆነውም ከቤታቸው ጀርባ በሚገኘው ሰርቪስ ቤት ውስጥ እህቱ ከጓደኛዋ ጋር ወሲብ እየፈፀመች ትገኛለች።ያየውን ማመን ያቃተው እንደሚወንድሟ እንደሚለው እየተደፈረች መስሎታል።
እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ እየጮኸ ወደ ሰርቪሱ መሄድ ይጀምራል። የእህቱ ጓደኛም ይደነግጥና ሮጦ ሊያመልጥ ይሞክራል። ከቤታቸው እንዳልወጣ እርግጠኛ የሆነው ወንድም በፍጥነት ከምግብ ማብሰያቸው ክፍል ረጅም ስለት ቢላ ይዞ የእህቱን ጓደኛ መፈለግ ይጀምራል።

                        ምስል፦ ሟች ሪሳን
በመጨረሻም ጓደኛዋን የመኪና ማቆሚያ ቤታቸው ውስጥ ተደብቆ ያገኘዋል። ባገኘውም ግዜ ይዞት በነበረው ስለት ቢላ ሶስት ጊዜ ይወጋዋል። የእህቱ ጓደኛ የነበረው ሪሳን ኡዳያኩማርም ሆስፒታል ቢደርስም በግራ ደረቱ ላይ ስለተወጋ ህይወቱ አልተረፈም። ኩማር የዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበረ ሲሆን አስራ ስምንት አመቱም ነበረ።

ጓደኛዋን ለማንም ቤተሰብ ያላሳወቀችው እህቱም ምክንያት ነበራት። ከልጆቻቸው ጋር ከመጠን ያለፈ ቁጥጥር የሚያደርጉት ወላጆችዋ ከዚህ ቀደም አንድ ሰው አታሎ የእርቃን ፎቶ እንዳስላካትና አንድ ግዜም ሳይታሰብ ቤት ሲመጣ ያገኙት ወላጀችዋ በጊዜው 14 ዓመት የነበረችውን እህቱን ከቤት ካልወጣች ብለው ወስነው ይኸው ወንድሟ እንዳስጣላት ፍርድ ቤቱ ይሰማል።
ዳኛውም ሲናገር እህትህን ከቤት እንዳትባረር የጣርከውን አውቄያለሁ ወላጆችህን ግን እወቅሳለው ምክንያቱም ድርጊታቸው አንተን የአስተሳሰብ ተፅዕኖ እንዲደርስብህ በማድረጋቸው። ከመጠን ያለፈ ቁጥጥሩ እህትህም ጓደኛዋን እንዳታስጠዋውቅ አንም የተደፈረች እንዲመስልህ የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል።
ግራ ቀኙን የመረመረው የእንግሊዝ ፍርድ ቤትም ወንድምየው ላይ የሰባት ዓመት እስር አስተላልፏል።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!