የአዲስ አበባ ታሪክ
አዲስ አበባ በጊዜ ዓይን
• ከ18ኛው መቶ ክፍለዘመን በኋላ የሸዋ ግዛት ዋና ከተማ።
• በግምት ከ1855-1867/68/69 ዓ.ም. ወጨጫ፣ የረር እንዲሁም እንጦጦ አፄ ምኒሊክ፪ እና እቴጌ ጣይቱ ያረፉባቸው ቦታዎች።
• በ 1871ዓ.ም. አፄ ምኒሊክ አህመድ ግራኝ ያፈራረሰውን ቦታ የጎበኙበት።
• በ1873ዓ.ም. አፄ ምኒሊክ የሸዋን ዋና ከተማ ከአንኮበር ወደ እንጦጦ አመጡ።
• በ1875ዓ.ም. አካባቢ ጣይቱ ፍል ውሃ አካባቢ ቤት አስገነባች።
• በ1878ዓ.ም. የእንጦጦ ደቡብ ክፍል በይፋ የሰው መስፈሪያ ሆነ።
• ከ1880ዓ.ም.-1882ዓ.ም. አዲስ አበባ የኢትዬጵያ ዋና ከተማ መሆኗ ተረጋገጠ።
• በ1901ዓ.ም. አዲስ አበባ 70,000 ቋሚ ኗሪና ከ30,000-50,000 የሚጠጉ ጊዜያዊ ኗሪ ነበሯት።
• ከግንቦት 1928ዓ.ም.-1933ዓ.ም. የጣልያን የኢትዬጵያ ቅኝ ግዛት ዋና መምሪያ መቀመጫ።
• ግንቦት 1933ዓ.ም. አፄ ኃይለስላሴ ከነበሩበት እንግሊዝ አዲስ አበባ ገቡ።
• በ 1955ዓ.ም. አፄ ኃይለስላሴ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረት ከጣሩ በኋላ መቀመጫውም በ አዲስ አበባ እንዲሆን አደረጉ።
Comments
Post a Comment