የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች


ልባዊ ሃሴት የሚሰጡን 15 የፍቅር እውነቶች

አውነት ለመናገር ፍቅር ዕውር ነው ሚባለውና ወንዶች በጣም ከሴቶች ቀድመው ‘ አፈቅርሻለው’ ማለታቸው ይሰራል። ፍቅር በሰው ልጅ ስነ ልቦና፣ በሰውነት አካል እንዲሁም በታሪካችን ውስጥ በጣም ወሳኝ ነው። ከዚህ ቀጥሎ 15 የፍቅርን እውነታዎች እንይ፦

1. አይን ላይን መተያየት፦ አንድ ጥናት ለ 3 ደቂቃ አይን ለይን የተያዩ ፍቅረኞች ልባቸው በእኩል አይነት ፍጥነት ይመታል።
2. ፍቅር ፈጣን ነው፦ አንድን ሰው መውደድ አለመውደዳችንን ለመወሰን አራት ደቂቃ ብቻ በቂ ነው።
3. ፍቅር ሱስ ነው፦ ጥናቶች አንደሚሉት ፍቅር የያዘው ሰው አእምሮ ልክ ሱስ ከያዘው አእምሮ ጋር ተመሳሳይ ምልክት ያሳያል።

4. ካፈቀሩት ጋር መለያየት የሃቅ ልብ ይሰብራል፦ በጥናቶች መሰረት ፍቺ፣ መለያየት፣ መጋጨት፣ ክህደት የመሳሰሉት የልብ ስብራት ሲንድሮም የተባለ በሽታ ያስከትላሉ።
5. ፍቅር ያስጨንቃል፦ ፍቅር ሲይዘን ሴሮቶኒን የተባለው የደስታ ሰጪ ሆርሞን ቀንሶ ኮርቲሶል የተባለው ጭንቀት የሚያሰማ ሆርሞን ይጨምራል።
6. በህይወት ላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር ይቀየራል።
7. ፍቅር ህይወትን በጣፋጭ መልኩ እንድናይ ያደርጋል።
8. ጥቂት ሰዎች ፍቅር አይዛቸውም፦ ሃይፖፒቱታሪዝም የተባለ በሽታ ያለባቸው ሰዎች።
9. ሰውነታችን ‘ የፍቅር ደም ስር’ አለው፦ የቀለበት ጣታችን ቀጥታ ከልባችን ጋር የሚገናኝበት ደም ስር።

10. ሴቶች ቴስቴስትሮን ይወዳሉ፦ ገንዘብ፣ እውቀት፣ ክብር፣ ጨዋታ አዋቂ፣ የሚጥር ወንድ እንደሚወዱት ሁሉ የወንድነት ሆርሞን የሆነውን ቴስቴስትሮን በብዛት የሚያመነጭ ወንድ ይወዳሉ።
11. መሳሳብ ከድሮም ያለ ነው፦ ወንዶች ከእንቅስቃሴ ጋር የሚገናኝ የፍቅር ግንኙነት ሲፈልጉ ሴቶች ከ ትዝታና ጥሩ ጊዜን በማስታወስ መደሰት ይፈልጋሉ።
12. የተረጋጋ ያሸንፋል፦ ጊዜ ወስደው የተዋወቁና የተጋቡ በፍጥነት ተዋውቀው ከተጋቡ ይልቅ የሰመረ ትዳር ይኖራቸዋል።

13. ፍቅር ሂደት ነው፦ አንድ ጥናት ጥንዶች ከመጋባት በፊት ሰባት ጊዜ ይፋቀራሉ።
14. ተቃራኒ አይዘልቅም፦ ተመሳሳይ መልክና የህይወት ዘዬ ያላቸው ጥንዶች በጣም ከሚለያዩ ጥንዶች የተሻለ ይዘልቃሉ።
15. ፍቅርና ሴክስ የተለያየ ነገር ያሳስቡናል፦ እንደ አጥኝዎች ከሆነ ፍቅር ፈጠራንና አርቆ አሳቢነትን ሲጨምር ሴክስ ደግሞ የቅርብ ውሳኔንና ጊዜያዊ ደስታን ብቻ እንድናስብ ያደርገናል።

Comments

Popular posts from this blog

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች