ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!
ሰባቱ የዓለም ህዝብ ሁሉ የሚስማማባቸው የሰብአዊነት መገለጫዎች
ጥናቱን ያካሄዱት ሳይንቲስቶች እንደሚሉት የዓለም ህዝብ ሁሉ በራሱ ማህበረሰብ ውስጥ የሚጋራቸውን ማህበራዊ ችግሮችን የሚፈታባቸው ሞራላዊ ህጎች ተመሳሳይ ናቸው። ጥናቱን በተለያየ የዓለማችን ክፍል ስልሳ የተለያየ ባህልና አኗኗር የሚከተሉ ማህበረሰቦች ነው ሳይንቲስቶቹ ያከናወኑት።
ሁሉም የዓለም ማህበረሰብ ሰባቱን ባህሪያት ጥሩ በመሆናቸው ተስማማምቶ የትኛው ከየትኛው እንደሚቀድም ብቻ ነው ያለያያቸው። ጥናቱን ያከናወነው የኦክስፎርድ ዮኒቨርስቲ አንትርፖሎጂ መምህር የሆኑት ዶ/ር ኦሊቨር ሲናገሩ ‘ እስከዛሬ ሲያከራክር የነበረው የሰብዓዊነት ባህሪያት በሰው ዘር ሁሉ መመሳሰል ትንሽ መልስ አግኝቷል ካሉ በኋላ ‘ እንደገመትነውም እነዚህ ሰባት የሰው ባህሪያት በመላው ዓለም ተቀባይነትና ክብር ያላቸው ባህሪያት ናቸው።’ ብለዋል።
ሰባቱ ህገ ባህሪያትም፦
1. ቤተሰብህን እርዳ
2. ከአጋሮችህ ጋር ተረዳዳ
3. ውለታ መልስ
4. ብልህ ሁን
5. ለታታላላቆች ታዘዝ፤ አክብር
6. ሀብትን በኀላፊነት ተጠቀም
7. የሌሎችን ንብረት አትንካ
Comments
Post a Comment