5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች


ከፍቅር ጓደኛ ጋር በፍፁም የማያወሯቸው አምስት ርዕሶች
በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ግልፅነት እጅግ ወሳኝ ነው። ጓደኛ ሆነን የምንደባበቀው ነገር መኖር የለበትም ይህም በተለይ እሩቅ ለመጓዝ ላሰብን ጥንዶች ትክክል ነው። ነገር ግን ቀጥሎ የምንመለከታቸው ርዕሶች ሳይነኩ ቢቀመጡ ይሻላል ምክንያቱም በተፈጥሮ ወንድና ሴት ይህን ዓለም የሚመለከቱበት መነፅር መቼም አንድ አይሆንምና።
1. ፖለቲካ፦

ፖለቲካ ማለት አንድ ማህበረሰብ አምኖ የሚቀበለው ወይም የተስማማበት ጉዳይ ሲሆን ለብቻ እንደ ጥንድ ማውራቱ የሚያመጣው ውጤት አናሳ በመሆኑ። በተለይ የፖለቲካ አቋማችሁ ከተለያየ ደግሞ አስቡት። ስለዚህ ፖለቲካዊ ወሬ አያስፈልግም።
2. ዘር፦

የሰው ልጅ ለመዋደድ መስፈርቱ ከውጪ ብቻ የሚታይ ሳይሆን መንፈሳዊም ነው በተለይ የእውነት የምትዋደዱ ከሆነ። ስለዚህ በዚህ ዓለም ሰልጥኖ እየተቀላቀለ ባለበት ወቅት ስለ ዘር ወሬ አንስቶ ከምናፈቅራት ጋር ከመለያየት ዝምታው አይሻልም። አስተሳሰብ ተለዋዋጭ ነውና የፍቅር ግንኙነት ደግሞ የፀና።
3. ስጦታ፦

ስጦታ ለሰው ልጅ አስደሳች ነገር ነው። ስጦታው ደግሞ ከምንወደው ሰው ሲሆን ትርጉሙ በጣም ብዙ ነው። እንደውም ስጦታ ቢሰጥ ሚመከረው በበዓል ወይም በታቀደ ዝግጅት ላይ ሳይሆን፣ ይቅር ማለት አይደለም፣ በድንገት ቢሆን እጅግ ውብ ነው። ድንገት መሆኑ ሁለት ነገር ይናገራል ለሚሰጠው ሰው አንድ እንደምታስቡላቸው አንዲሁም በጥልቅ እንደምታውቋቸው ይመሰክራል። በነገራችን ላይ ስጦታ መስጠት ወይስ መቀበል በጣም የሚያስደዐስተው?
4. የጓደኛን ሚስጥር፦

ሁለታችሁም የምታውቁት ሰው ይሁን ወይም ለብቻ የጓደኛ ሚስጥር መጠበቅ አለበት። ጓደኛችሁ ሚስጥር ያካፈላችሁ ስለሚተማመንባችሁ ነውና ሚስጥሩ ሚስጥር መሆኑ እስኪያቆም ሚስጥር መጠበቅ አለበት። የሚስጥርነቱ ማቆም ምክንያት መሆን የለባችሁም።
5. ስለቀድሞ ፍቅረኛ፦

መቼም ግንኙነት ሳይጠብቅ ስለቀድሞ ፍቅረኛ ታሪክ ማውራት ያለ ነው። ጊዜ ካለፈና የናንተ ግንኙነት እየሰመረ ከመጣ የድሮ ፍቅረኛ ታሪክ በቃ የተቆለፈበት መሆን ይገባዋል። በጓደኛቹ ላይ የመጠራጠር ሀሳብ ከማምጣቱም በላይ ጓደኛቹም ስለ ቀድሞ ግንኙነት እንዲያስብና ያልተጠበቀ ውጤት እንዲመጣ መንገድ ትከፍቱ ይሆናል።

Comments

Popular posts from this blog

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች