ነነዌ

ነነዌ በኦሪት ዘፍጥረት 10፡11 መሠረት የሴም ልጅ አሦር ከሰናዖር ወጥቶ ነነዌንና ሌሎችን ከተሞች ሠራ። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ግን ከፊተኛው ቁጥር ከ10፡10 በመውሰድ አድራጊው እንደ ናምሩድ ቆጥረውት፣ ናምሩድ እራሱ ወደ አሦር (ወደ ሀገሩ) ወጥቶ እኚህን ከተሞች እንደ ሠራ ይላሉ። በጥንታዊ የግሪክ ታሪክ ጸሃፊዎች ዘንድ ኒኑስ የነነዌ መስራችና የአሦር መጀመርያ ንጉስ ነበረ። ነነዌ ከጥንት ጀምሮ ከአሹር ከተማ-አገር ይገዛ ነበር። እንደ አሹር ከ1440 እስከ 1366 ዓክልበ. ድረስ በሚታኒ ይቆጣጠር ነበር። ትልቅ ከተማ ነበረ። በ775 ዓክልበ. አካባቢ ነቢዩ ዮናስ ወደ ነነዌ ሂዶ የአሦር ሰዎች ወደ ንሥሐ እንዳመጣቸው በመጽሐፈ ዮናስ ይገለጻል። የዮናስ መቃብር የሚባለው የተቀደሠ መስጊድ በነነዌ (የአሁኑ ሞሱል) አካባቢ ይገኝ ነበር፤ በሐምሌ 2006 ዓ.ም. የኢስላማዊ ተዋጊዎች ከ«ኢስላም ግዛት በኢራቅና ሶርያ» ወገን የዮናስን መስጊድ አፈረሱት። በ713 ዓክልበ. ንጉሥ ሰናክሬም የአሦርን ዋና ከተማ ወደ ነነዌ መለሠው።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች