ምን ያህል ጊዜ አለን?
ምን ያህል ጊዜ አለን?
ባለፈው ሳምንት ጠዋት አርፍጄ በመነሳቴ ሻወርም ሳልወስድ፣ ቀርስም ሳልበላ፣ ኚጃማያን አውልቄ፣ በቅርብ ያገኘሁትን ልብስ ለብሼ ትንሽ ደቂቃ መስታወት ጋር አሳለፍኩና ከቤት ወጣው። መቼም የ 5 ደቂቃ ልዩነት በታክሲ ሰልፍ ላይ የሚያመጣውን ልዩነት የሚያውቅ ያውቀዋል። ያቺ የ 5ደቂቃ ልዩነት፣ ከቤቴ ምወጣበት ማለት ነው፣ የአንድ ሰዓት ማርፈድ አስከተለች እላችዋለው። ከዛም የአዲስ አበባ ኗሪ እንዴት ነው ጊዜውን ሚያብቃቃው ብዬ የተወሰነ ቀላል ጥናት ለማድረግ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ስጠይቅ ያገኘሁትን መልሶች አካፍዬ በኋላ አጠቃልለዋለው፦
ጥያቄ፦ ለስንት ሰዓት ትተኛለህ?
ሰለሞን፦ 7-8 ሰዓት
ጥያቄ፦ በቀን ስንት ሰዓት ትሰራለህ?
ሰለሞን፦ ነጋዴ ስለሆንኩ ከ8-10 ሰዓት
ጥያቄ፦ ቀሪ 6 ሰዓት አለህ፣ ምን ታደርግበታለህ?
ሰለሞን፦ እንደቀኑ ቢለያይም ስራ ስመጣ 1 ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ወደ ቤት ስመለስም እንደዛው ስለሚወስድ የሚተርፈኝ ሦስት ሰዓት ብቻ ነው። በሱም ሁለት ፊልም አይቼ ጨርሰዋለው።
ጥያቄ፦ ለስንት ሰዓት ትተኛለሽ?
ሐምራዊት፦ 5 ሰዓት
ጥያቄ፦ በቀን ስንት ሰዓት ትሰሪያለሽ?
ሐምራዊት፦ እየተማርኩ ነው። የምማርበት ሰዓት ደሞ እንደ ቀኑ ኘሮግራም ይለያያል። በአማካይ ግን 5 ሰዓት ክላስ ውስጥ ነኝ።
ጥያቄ፦ ብዙ ሰዓት ይተርፍሻል ማለት ነዋ አይደል?
ሐምራዊት፦ ኧረ ምንም ሰዓት አይተርፍም ጥናቱ፣ አሳይመንቱ፣ ትራንስፖርቱ፣ ምናምን በቃ ሁልጊዜ ጊዜ ያጥረኛል ስለዚህ ጊዜ አይተርፈኝም።
ጥያቄ፦ ለስንት ሰዓት ትተኛለሽ?
ሜሮን፦ 7-8 ሰዓት
ጥያቄ፦ ለስንት ሰዓት ትሰሪያለሽ?
ሜሮን፦ 8 ሰዓት
ጥያቄ፦ የቀረውን ስምንት ሰዓትስ?
ሜሮን፦ መጀመሪያ በመንገድ ላይ 2ሰዓት ይጠፋል፣ ትምርት ስለምማር መሄዱ ክላስ ትምርቱ ምናምን 3ሰዓት ይወስዳል የቀረችው ሰዓት ደግሞ ምግብ መስሪያ፣ ልጄን መንከባከቢያ ምናምን ስል በቃ ቀኑ ያልቃል።
ጥያቄው ስራ ወይም ትምርት ላይ ያሉ ብቻ የመለሱት ቢሆንም የሚነግረን ነገር ግን አለ ለምሳሌ የሦስቱንም ሰዓት የሚወስድ የጋራ ነገር ምናምን። ሆኖም ግን በስራ ላይ ላለ ሰው የምትተርፈውን ሰዓት በብልሀት በመጠቀም ደስተኛ ህይወት እንዲኖረው እንዲያደርግ መክራለው።
Comments
Post a Comment