አያስቀኑም?
ጀስቲን ቢበርና ሀይሊ ባልድዊን
ሁለቱ ወጣቶች በየመስካቸው እጅግ ስኬታማ ከሚባሉት ወጣት ባለተሰጥዖዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ። ጀስቲን በካናዳ ሲወለድ እናቱ እጅግ ተቸግራ ለብቻዋ አሳደገችው። በዮቲዩብ ቪዲዬ በመልቀቅ የጀመረው የህይወት ጥሪው በቢልቦርድ በርካታ ጊዜ አንደኛ በመሆን በ ዩኤስ አሜሪካም ትሪኘል ኘላቲነም ያገኘ አልበም በመሥራት እንዲሁም በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች በጣም ብዙ ተከታይ ካላቸው ሰዎች አንዱ ነው።
ሀይሊ በበኩሏ ደሞ ከታዋቂው የአሜሪካ አክተር ስቴፈን ባልድዊን በቱሰን አሪዞና ዩኤስ ስቴት ተወለደች። ሀነይሊ የሞዴሊንግ ባለሞያ ስትሆን ከተለያዩ ታዋቂ የፋሽንና ሞዴሊንግ ድርጅቶች ጋር ትሰራለች። ለምሳሌ ከቮግ መፅሔት ጋር፣ ከራልፍ ሎረን፣ ከ ደልቺ ኤንድ ጋባና፣ እናም ከበርካታ ሌሎች ድርጅቶች ጋር ትሰራለች። በተጨማሪም በተወሰኑ ፊልሞች እንዲሁም የቲቪ ዝግጅቶች ላይ ትሰራለች። ስለ ህይወቷ ስትጠየቅ እንዲህ ብላ ነበረ ‘ እኔ ቤተክርስቲያን ነው ያደኩት፣ ከፈጣሪ ጋር ሁሉም ሰው ግንኙነት እንዲኖረው መክራለው። እግዚአብሔር ያረገልኝን ሀሌም አስባለው እናም የህይወቴ ስኬት ሁሉ በእርሱ እንደሆነም አምናለው’ ብላ ነበረ።
ባለፈው አመት ህደር 23 2018 ላይ ትደር የመሰረቱት ጥንዶች መጀመሪያ ከሁለት ዓመት በፊት ፍቅር ቢጀምሩም ከወራት በዋላ ተለያይተው ነበረ። ከዛም ግንቦት 2018 ላይ ድጋሚ ፍቅር ጀምረው ከነጭራሹም በ ስድስት ወር ውስጥ ለትዳር በቅተዋል። ምን ያህል ይዘልቁ ይሆን? አብረን እናያለን።
Comments
Post a Comment