ጊዜያችን ምንድነው?


ጊዜ
ጊዜ የማያቋርጥና የማይቀለበስ የነገሮችና ሁኔታዎች መፈጠርና መቀየር ሂደት ነው። ጊዜ ካለፈው ተነስቶ በ አሁን ውስጥ አልፎ ወደ ነገ የሚያመራ ነው።

ጊዜ የሁሉም ሳይንስ፣ ሀይማኖት፣ ፊሎዞፊ ወዘተ የመለኪያ ግብዓት ነው። ጊዜን ሳያገናዝቡ የሚተገበር ነገር የለም። የሰው ልጅ በሙሉ በብዛት እንዲኖረው የሚፈልገው ነው። ለምሣሌ ዛሬ የነበረኝን ኘሮግራም ልናገር፦  ጠዋት 1 ሠዓት ከአልጋ መውረድ፣ ሻወር መውሰድ፣ቁርስ ማዘጋጀት ፣ ሻይ መፍላት፣ መመገብና መጠጣት፣ 2:10 አካባቢ ከቤት መውጣት 3:00 አካባቢ ስራ መግባት( ከዚህ በኋላ እስከ 11:00 የስራዬ ሰዓት ነው)፣ 12:00-2:00 ሰዓት አካባቢ የሶሻል ሚዲያ ስራ ሰራለው ። ከዛም 3:00 ሰዓት አካባቢ ቤት እደርሳለው። ፀጉሬ አልተሰራም፣ እራቴ አልተሰራም፣ አልጋዬ አልተነጠፈም፣ የመሳሰሉት። አዎ ብዙዎቻችን ቢያንስ ሰራተኛ ቀጥረን ትንሽ ፋታ እናገኛለን፣ የነሱን ጊዜ ገዝተን ማለት ነው።

የአሁኑን የጊዜ ወሬ አንድ ነገር ብዬ ልዝጋው፣ የአዕምሮ  አነቃቂ  ነገሮች ለምሳሌ ሻይ፣ ቡና ምናምን ጊዜ በጣም እየፈጠነ እንደሆነ እንድናስብ ሲያደርጉ፣ የአዕምሮ አድካሚ ነገሮች ለምሳሌ አልኮሆል፣ ጊዜ ቀስ እያለ እንደሆነ እንድናስብ ያደርጉናል። ስለዚህ ከአነቃቂም ሆነ ከአድካሚ የአዕምሮ ምግቦች ነፃ ሆነን ጊዜያችንን እንዳኝ።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች