አብሮ መመገብ፤ ኀላ ቀር ባህላችን


አብሮ መብላት
ምሳ ሰዓት መድረሱን ጓደኛዬ ስትነግረኝ አላመንኩም ሰዓቱ እንዴት ይሮጣል ብዬ እያሰብኩ ሳለ ዛሬ የእርሷ ጓደኛ መቅደስ አብራን እንደምትበላ ለማሳወቅ ‘መቅዲም አብራን ነው ምትበላው’ስትል ከሀሳቤ ነቅቼ ከወንበሩ እየተነሳው አብሮ መብላት የሚባለው ዕንቁ ባህል እየቀረ መሆኑ ትዝ አለኝ።
ዘመናዊነት ከሚገለፅባቸው መንገዶች አንዱ ምቾት የሚነሱና አድካሚ ስራዎችን ማሻሻል ነው። ወይም ደግሞ ሁኔታዎችን የምንረዳበትንና የምናስተናግድበትን መንገድ በተሻለ መንገድ መቀየስ ነው። ለምሳሌ እንጀራን በመሶብ ከመብላት ንፅህናው በቀላሉ በሚጠበቅ የኘላስቲክ ሳህን መመገብ ዘመናዊነት ነው። ወጥን በሸክላ ደስት ከመስራት ይልቅ በ ብረት ድስት መስራት ሀይል እና ጊዜ ስለሚቆጥብ ምርጫችን ዘመናዊ ነው።

እስኪ አሁን አብሮ መብላት ዘመናዊ ወይም ኋላ ቀር መሆኑን እንገምግመው። የሆነ ቀን ወንድሜን ቁርስ አብረን እንብላ ስለው ከሰው ጋር መብላት ጊዜ እንደማባከን እና ምንም ጥቅም ያለው እንደማይመስለው እንደ ቀልድ እየነገረኝ ሻዩንና ምግቡን ይዞ ወደ ቲቪው ጋር ሄደ። ወንድሜ እራሱን እንደዘመናዊ ሰው ስለሚያይ አብሮ መብላትን እንደ ኋላ ቀር ባህል ባይቆጥር አብሮኝ ይሆን ነበረ። ምክንያቱም የምንገናኘው በወር ምናምን ስለሆነ ብዬ ነው። አብሮ የመብላት ባህላችን እየጠፋ ባይሆን ኖሮ ከወንድሜ ጋር ስለ ሰራችን ስለ ገጠሙን ችግሮችና መፍትሄዎች እያወራን ደስ ብሎን እንበላ ነበረ። ነገር ግን ሆዳችንን ብቻ ለብቻችን ሞልተን ወደየፊናችን ለብቻችን።

አብሮ መብላት ሲባል የግድ በአንድ ሳህን አንድ አይነት ምግብ መሆን አለበት ማለትኮ አይደለም። ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት ጓደኛዬ የልጁን ልደት ሲያከብር ትልቅ የምግብ ቡፌ አዘጋጅቶ ነበረ፤ ለምን ብዬ ጠየኩት ትንሽ የበዛ ስለመሰለኝ።እርሱም ‘የልጄን ልደት ልታከብሩ ስትመጡ ደስታዬን የማካፍላቹ ጥሩ ጥሩ ምግብ ተዘጋጅቶ አብሬያችው እየበላው መሆኑ መንፈሳዊ ደስታ ይሰጠኛል’ አለኝ።

ብዙዎቹ ታላላቅ የአለም ኩባንያዎች ለምሳሌ ጉግል፣ ፎርድ መኪና ማምረቻ የመሳሰሉት ሰራተኞች አብረው በመብላታቸው ምርታማነታቸው እንደሚጨምር ስለተረዱ፣ ምሳ የሚበላበት ያማረ አዳራሽ አዘጋጅተው የተመረጠ የጣፈጠ ምግብ በነፃ ያቀርባሉ።
ብዙዎች መሪዎች አብሮ የመብላትን ጥቅም ስለሚረዱ ሊጎበኛቸው የመጣን እንግዳ የሚያወያዪት ምግብ አብረው እየተመገቡ ነው። ይህም የሆነው አብሮ መብላት የሚጠቅምና የማይተካ ኀይል እንዳለው ስኬታማ ሰዎች ስለተረዱት ነው። ለእኛ ግን ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ባህል ኋላ ቀር ሆነ?

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች