ኀላፊነት አለብኝንዴ??


የአስራ አንድ አመቷ ማላላ ዩሳፍዛይ በጊዜው ታሊባን ይቆጣጠረው በነበረው የሰሜን ምስራቅ ፖኪስታን ክፍል ትኖር ነበረ። ታሊባን ቴሌቭዥን፣ ፊልም፣ ስፖርት፣ የሴቶችን ነፃነት በሙሉ በአዋጅ ከለከለ።

ይህ ያልተዋጠላት ማላላ በግልፅ መቃወም ከመጀመሯም በላይ ሴቶች እንዳይማሩ የከለከለውን አዋጅ ባለመቀበል ታሊባን በማይቆጣጠረው የፖኪስታን ክፍል እየሄደች ትምህርት  እንደምትማር ታሊባን ይደርስበታል። በ2009እኤአ አንድ ቀን ትጓዝበት የነበረው አውቶቡስ በድንገት ይቆማል፣ ከዛም በኋላ አንድ ግማሽ ፊቱን በጨርቅ የሸፈነ ሰው መሳሪያውን እያቀባበለ ወደ አውቶቡሱ በመግባት ‘ ማላላ ምትባለው ማን ናት’ ብሎ ተሳፋሪዎቹ ላይ መሳሪያውን ይደግናል። ማላላም ምንም ሳትፈራ ‘ ማላላ እኔ ነኝ’ ትለዋለች፣ ሰውየውም ወደርሷ ቀርቦ ፊቷን በጥይት መቶ ይሰወራል። መቼም የማላላ ታሪክ ከዚህ በኋላ ታዋቂ ሆኗል እንደውም የኖቤል ተሸላሚ ሁሉ ሆናለች።

ለምንወስዳቸው የህይወት ውሳኔዎች ኅላፊነት ሊሰማን እንደሚገባና ለሚከተለውም ውጤት እራሳችን ተጠያቂ መሆናችንን ነገር ግን ይህንን በማድረጋችን ደሞ ጊዜያዊ ችግር ሊገጥመን እንደሚችል፣ ሆኖም ግን የተሻለ እድልና ውጤት ደግሞ ሊመጣ እንደሚችል ከማላላ ታሪክ መማር ይቻላል። ማላላ አደጋ እንዳይደርስባት ማድረግ ባትችልም የተከሰተባትን ችግር ኀላፊነት በመውሰድ የተሻለ ውጤት አግኝታለች ።

አያድርስና ንብረታቹ መዘረፋን ባወቃቹበት ቅፅበት በእምሯቹ የሚመጡትን የተለያዩ ሀሳቦች፣ ለምሳሌ ድርቅ ማለት በድንጋጤ፣ መጮህ፣ ሌባውን ማሳደድ፣ የመሳሰሉት ምርጫዎች ለተከሰተባቹ ችግር በምን መልኩ ኀላፊነት ለመውሰድ እንደወሰናቹ ያመለክታል። መሰረቁን ባትፈልጉትም ከተከሰተ ግን ወደዳቹም ጠላቹ የችግሩ መፍትሄ በናንተ ላይ ነው።

የምንኖርባት ዓለም ሁሌም ችግር ትፈጥራለች፣ ችግሮቹም ወይ ወደንና ፈቅደን ያመጣናቸው ወይም ደግሞ ከቁጥጥራችን ውጪ በሆኑ ክስተቶች የመጡ ይሆናሉ። ዋናው ነገር መቼም የማይቀረውን ችግር ኀላፊነት ወስዶ መፍታት ከዛም ደግሞ ሁሌም ካለም ላይ ለማይቀረውና ለሚከሰትብን ሌላ አይነት፣ ችግርና መፍትሄ መዘጋጀት ነው።

Comments

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች