Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps February 25, 2019 Samsung galaxy amp prime 3 5GB speed, 10GB capacity, 8MP rear camera, 5MP front camera Price- 5400.00 ( Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Comments
5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች March 06, 2019 ከፍቅር ጓደኛ ጋር በፍፁም የማያወሯቸው አምስት ርዕሶች በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ግልፅነት እጅግ ወሳኝ ነው። ጓደኛ ሆነን የምንደባበቀው ነገር መኖር የለበትም ይህም በተለይ እሩቅ ለመጓዝ ላሰብን ጥንዶች ትክክል ነው። ነገር ግን ቀጥሎ የምንመለከታቸው ርዕሶች ሳይነኩ ቢቀመጡ ይሻላል ምክንያቱም በተፈጥሮ ወንድና ሴት ይህን ዓለም የሚመለከቱበት መነፅር መቼም አንድ አይሆንምና። 1. ፖለቲካ፦ ፖለቲካ ማለት አንድ ማህበረሰብ አምኖ የሚቀበለው ወይም የተስማማበት ጉዳይ ሲሆን ለብቻ እንደ ጥንድ ማውራቱ የሚያመጣው ውጤት አናሳ በመሆኑ። በተለይ የፖለቲካ አቋማችሁ ከተለያየ ደግሞ አስቡት። ስለዚህ ፖለቲካዊ ወሬ አያስፈልግም። 2. ዘር፦ የሰው ልጅ ለመዋደድ መስፈርቱ ከውጪ ብቻ የሚታይ ሳይሆን መንፈሳዊም ነው በተለይ የእውነት የምትዋደዱ ከሆነ። ስለዚህ በዚህ ዓለም ሰልጥኖ እየተቀላቀለ ባለበት ወቅት ስለ ዘር ወሬ አንስቶ ከምናፈቅራት ጋር ከመለያየት ዝምታው አይሻልም። አስተሳሰብ ተለዋዋጭ ነውና የፍቅር ግንኙነት ደግሞ የፀና። 3. ስጦታ፦ ስጦታ ለሰው ልጅ አስደሳች ነገር ነው። ስጦታው ደግሞ ከምንወደው ሰው ሲሆን ትርጉሙ በጣም ብዙ ነው። እንደውም ስጦታ ቢሰጥ ሚመከረው በበዓል ወይም በታቀደ ዝግጅት ላይ ሳይሆን፣ ይቅር ማለት አይደለም፣ በድንገት ቢሆን እጅግ ውብ ነው። ድንገት መሆኑ ሁለት ነገር ይናገራል ለሚሰጠው ሰው አንድ እንደምታስቡላቸው አንዲሁም በጥልቅ እንደምታውቋቸው ይመሰክራል። በነገራችን ላይ ስጦታ መስጠት ወይስ መቀበል በጣም የሚያስደዐስተው? 4. የጓደኛን ሚስጥር፦ ሁለታችሁም የምታውቁት ሰው ይሁን ወይም ለብቻ የጓደኛ ሚስጥር መጠበቅ አለበት። ጓደኛችሁ ሚስጥር ያካፈላችሁ ስለሚተማመንባችሁ ነውና ሚስጥሩ ሚስጥር መሆኑ እስኪ Read more
ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት! March 14, 2019 ሰባቱ የዓለም ህዝብ ሁሉ የሚስማማባቸው የሰብአዊነት መገለጫዎች ጥናቱን ያካሄዱት ሳይንቲስቶች እንደሚሉት የዓለም ህዝብ ሁሉ በራሱ ማህበረሰብ ውስጥ የሚጋራቸውን ማህበራዊ ችግሮችን የሚፈታባቸው ሞራላዊ ህጎች ተመሳሳይ ናቸው። ጥናቱን በተለያየ የዓለማችን ክፍል ስልሳ የተለያየ ባህልና አኗኗር የሚከተሉ ማህበረሰቦች ነው ሳይንቲስቶቹ ያከናወኑት። ሁሉም የዓለም ማህበረሰብ ሰባቱን ባህሪያት ጥሩ በመሆናቸው ተስማማምቶ የትኛው ከየትኛው እንደሚቀድም ብቻ ነው ያለያያቸው። ጥናቱን ያከናወነው የኦክስፎርድ ዮኒቨርስቲ አንትርፖሎጂ መምህር የሆኑት ዶ/ር ኦሊቨር ሲናገሩ ‘ እስከዛሬ ሲያከራክር የነበረው የሰብዓዊነት ባህሪያት በሰው ዘር ሁሉ መመሳሰል ትንሽ መልስ አግኝቷል ካሉ በኋላ ‘ እንደገመትነውም እነዚህ ሰባት የሰው ባህሪያት በመላው ዓለም ተቀባይነትና ክብር ያላቸው ባህሪያት ናቸው።’ ብለዋል። ሰባቱ ህገ ባህሪያትም፦ 1. ቤተሰብህን እርዳ 2. ከአጋሮችህ ጋር ተረዳዳ 3. ውለታ መልስ 4. ብልህ ሁን 5. ለታታላላቆች ታዘዝ፤ አክብር 6. ሀብትን በኀላፊነት ተጠቀም 7. የሌሎችን ንብረት አትንካ Read more
የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች March 15, 2019 ልባዊ ሃሴት የሚሰጡን 15 የፍቅር እውነቶች አውነት ለመናገር ፍቅር ዕውር ነው ሚባለውና ወንዶች በጣም ከሴቶች ቀድመው ‘ አፈቅርሻለው’ ማለታቸው ይሰራል። ፍቅር በሰው ልጅ ስነ ልቦና፣ በሰውነት አካል እንዲሁም በታሪካችን ውስጥ በጣም ወሳኝ ነው። ከዚህ ቀጥሎ 15 የፍቅርን እውነታዎች እንይ፦ 1. አይን ላይን መተያየት፦ አንድ ጥናት ለ 3 ደቂቃ አይን ለይን የተያዩ ፍቅረኞች ልባቸው በእኩል አይነት ፍጥነት ይመታል። 2. ፍቅር ፈጣን ነው፦ አንድን ሰው መውደድ አለመውደዳችንን ለመወሰን አራት ደቂቃ ብቻ በቂ ነው። 3. ፍቅር ሱስ ነው፦ ጥናቶች አንደሚሉት ፍቅር የያዘው ሰው አእምሮ ልክ ሱስ ከያዘው አእምሮ ጋር ተመሳሳይ ምልክት ያሳያል። 4. ካፈቀሩት ጋር መለያየት የሃቅ ልብ ይሰብራል፦ በጥናቶች መሰረት ፍቺ፣ መለያየት፣ መጋጨት፣ ክህደት የመሳሰሉት የልብ ስብራት ሲንድሮም የተባለ በሽታ ያስከትላሉ። 5. ፍቅር ያስጨንቃል፦ ፍቅር ሲይዘን ሴሮቶኒን የተባለው የደስታ ሰጪ ሆርሞን ቀንሶ ኮርቲሶል የተባለው ጭንቀት የሚያሰማ ሆርሞን ይጨምራል። 6. በህይወት ላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር ይቀየራል። 7. ፍቅር ህይወትን በጣፋጭ መልኩ እንድናይ ያደርጋል። 8. ጥቂት ሰዎች ፍቅር አይዛቸውም፦ ሃይፖፒቱታሪዝም የተባለ በሽታ ያለባቸው ሰዎች። 9. ሰውነታችን ‘ የፍቅር ደም ስር’ አለው፦ የቀለበት ጣታችን ቀጥታ ከልባችን ጋር የሚገናኝበት ደም ስር። 10. ሴቶች ቴስቴስትሮን ይወዳሉ፦ ገንዘብ፣ እውቀት፣ ክብር፣ ጨዋታ አዋቂ፣ የሚጥር ወንድ እንደሚወዱት ሁሉ የወንድነት ሆርሞን የሆነውን ቴስቴስትሮን በብዛት የሚያመነጭ ወንድ ይወዳሉ። 11. መሳሳብ ከድሮም ያለ ነው፦ ወንዶች ከእንቅስቃሴ ጋር የሚገናኝ Read more
Comments
Post a Comment