ውዱ ሰዓት የትኛው ነው?
የዓለማችን የመጨረሻ ውድ ሰዓቶች
በዚህ ዘመን መቼም በአብዛኛው ሰው ዘንድ ሰዓት ማሰር እየቀረ ነው። መንገድ ላይ ሰዓት ስትጠይቁ የጠየቃቹት ሰው እጁን ወደ ኪሱ ወይም ቦርሳዋ ከቶ ስልኩን አውጥቶ አይቶ የሚናገር ነው የሚበዛው። ቢሆንም በዚህ ዘመንም ውድ ዕቃ የመሰብሰብ ፍላጎት ያለው ወይም ደግሞ በድሮ ወግ መኖር የሚፈልግ ኀብታም ስላለ ነው የሚቀጥሉት ሰዓቶች እጅግ በውድ የተሸጡት።
6. ሮሌክስ ዳይቶና፣ 17.8 ሚሊየን ዶላር፦
የድሮው አክተር ፖውል ኒውማን ለ13 ዓመት ያሰረውና ከሚስቱ በስጦታ የተበረከተለት ሰዓት ሲሆን ለ13 ዓመት በየቀኑ ቢያስረውም እንደ አዲስ ሆኖ ነው ያለው። ለልጁ የወንድ ጓደኛ በስጦታ የሰጠው ሲሆን ልጁም ሰዓቱን ለጨረታ አቅርቦ ማንነቱ ላልተጠቀሰ ገዥ ተሽጧል።
5. ፓቴክ ፍሊፔ ሔንሪ ግሬቭስ ሱፐርኮምፕሊኬሽን 24 ሚሊየን ዶላር፦
ይህ የኪስ ሰዓት ለዲዛይን 3 ዓመት ለመሰራት ደግሞ ሌላ አምስት ዓመት ወስዷል። በተሰራበት ዘመን 1930 እጅግ የረቀቀ አሰራር እንዳለው የሚነገርለት ሰዓት በ 1999 11ሚሊየን ዶላር ሲሸጥ ጉድ ተብሎ ነበር። አሁን ደግሞ የባሰ ዋጋው ጨምሮ 24 ሚ. ዶላር አውጥቷል።
4. ቾፓርድ 201 ካራት 25 ሚሊየን ዶላር፦
ይህ ሰዓት 800 የተለያየ ቀለምና ቅርፅ ያላቸው ዕንቁዎች አሉት። በሚስጥር የሚታወቅ ቁልፍ ሲጫኑ ደግሞ አንድ ሰማያዊ፣ አንድ ግራጫ እና አንድ ሮዝ ቀለም ያላቸው የዕንቁ ልብ ቅርፆች ብቅ ይላሉ። የሰዓቱ ውስጥ መደብ ላይ የሚገኙት ዕንቁዎች ሰዓት ስትመለከቱ ቢጫ ብርሃን በመስጠት ውበቱን ይጨምራሉ።
3. ጃገር ሌኩት ጆዌል 101 ማንቼት 26ሚሊየን ዶላር፦
መጀመሪያ ሲመለከቱት ብራስሌት ብቻ የሚመስለው አተኩረው ሲያዩት ትንሽዬ ሰዓት እንዳለች ይረዳሉ። ይህ ሰዓት የዓለማችን ትንሹን የሜካኒካል እንቅስቃሴ ሪከርድ እንደያዘ ነው።
2. ብሬጉት ግራንድ ኮምፕሊኬሽን 30ሚሊየን ዶላር፦
ባለ ብዙ ታሪኩ ይህ ሰዓት ከእየሩሳሌም ከተዘረፈ በኃላ በ20 ዓመቱ የተገኘ ሰዓት ሲሆን በተሰራበት በ 18ኛው ክፍለ ዘመን ሁሉንም የዘመኑን ጥራት እንዲጠብቅ ተደርጎ ነው።
1. ግራፍ ዳይመንድስ ሀሉስኔሽን 55 ሚሊየን ዶላር፦
ግራፍ ዳይመንድስ ማለት በዓለማችን የታወቀ የጌጣጌጥ ደርጅት ሲሆን ብዙ እንደተለፋበት የሚነገረው ይህ ሰዓት የተለያየ ቀለምና ቅርፅ ያላቸው ዕንቁዎች አሉት። በተካኑ ባለሙያዎች ብዙ ሺህ ሰዓት የወሰደው ይህ ሰዓት በ2014 ሲጠናቀቅ እጅግ የሚስብና ውብ ሆኖ የዓለማችን ውዱ ሰዓት ተብሏል።







Comments
Post a Comment