Ethiopian mother of hostess speaks/ ልጅ ሳታስመኝ ተለየችኝ
የሆስተሷን እናት ሀዘን እጥፍ ያደረገው......
' ሁልጊዜ ስትወጣ እማዬ ቻው ብላ ስማኝ ነው የምትወጣው' አሉ ወይዘሮ ክበብዋ ለገሰ የ ሆስተሷ እናት ሲናገሩ። ' የዛን ቀን ግን ረፈደባትና አልሳመችኝም ነበር' አሉ ለቢቢሲ ሲናገሩ።
በአካባቢው ኗሪ ' ክፉ ቦታ' ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የወደቀው አውሮኘላን አስተናጋጅ የነበረችው አያንቱ ግርማዬ 24 ዓመቷ ነበር። በቤተሰቧ ዘንድ እጆግ ተወዳጅ የነበረችው አያንቱ ለአባቷ ልዩ ፍቅር ነበራት።
ያለፈው እሁድ የቀብር ስነስርዓት የተደረገላቸው ኢትዩጵያውያን በሙሉ ባዶ ሳጥን እንደተደረገ የሚታወቅ ሲሆን፣ ወ/ሮ ክበቧ ሲናገሩ ' ባዶ ሳጥንም ቢሆን እንኳን ከሌሎቹ ተለይታ እንድትቀበር አልፈልግም' ካሉ በኋሏ ' የቀብር ስነስርዓቱ እንዲቆርጥልኝ አድርጓል' ብለዋል።
' ካንዴም ሁለቴ በቦታው ሄጄ ከጣርቻለው የተረዳሁትም የልጄን ምንም ነገር ማግኘት እንደማልችል ነው' ካሉ በኋላ በእንባ እየራሱ 'የሚቆጨኝ ' አሉ 'የሚቆጨኝ መካሻ የሆነ ልጅ እንኳን ትታ አለመሄዷ ነው' ብለዋል።
ለወ/ሮ ክበቧ መፅናናትን ለ አያንቱ ደግሞ አፀደ ገነትን እንመኛለን።
Comments
Post a Comment