Family time with phones/ ሞባይል ስልክ የቤተሰብን አብሮነት ይጨምራል


ሞባይል ቤት ወስጥ መጠቀም የቤተሰብን ግንኙነት እምብዛም አይጎዳም፤ አንድ ጥናት

ያለፈውን 15 ዓመት በጥናቱ ያካተተው የእንግሊዝ የቤተሰብ ግንኙነት አጥኚዎች እንዳሉት ከሆነ የልጆችን ዴያሪ ወይም የቀን ውሎ ፅሁፍ፣ የወላጆችን ዲያሪ ከ2,500 ሰዎች ዋቢ አድርገው ነው ያጠኑት። በጥናታቸው ልጆችና ወላጆች የሚለያዩበትን የጊዜ መጠን፣ ቤት ውስጥ አብረው ግን ለየብቻቸው የሚሆኑበትን እንዲሁም ልጆችና ወላጆች አብረው ሆነው ወይ ሲመገቡ ወይ አብረው የቤት ስራ ሲሰሩ ወይም ደግሞ ቲቪ ሲያዩ የሚያሳልፉትን ጊዜ ከግምት አስገብተው ነው።

የጥናቱ ውጤት፦

  • ልጆችና ወላጆች በቀን ባንድላይ የሚያሳልፉት ሰዓት በ15 ዓመት ውስጥ በ 30 ደቂቃ ጨምሯል።
  • አብረው የሚያከናውኑት ተግባር ለምሳሌ አብሮ መብላት ወይም ቲቪ ማየት መጫወት የመሳሰሉት በ 3 ደቂቃ ብቻ ጨምሯል። ይህ ትንሽ ቢመስለልም አሉ አጥኝዎቹ ' ትንሽ ቢመስልም በዚህ ሁሉ የቴክሎኖጂ ጋጋታ ወላጆች ከልጆች ጋር የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ አጥብቀው ይፈልጉታል ማለት ነው' ብለዋል።
  • የቤተሰብ አባላቱ በአማካይ በቀን በአንድላይ የሚያሳልፉት ጊዜ ከ349 ደቂቃ በ 15 ዓመት ውስጥ ወደ379 ደቂቃ ቢያድግም ለየብቻቸው የሚያከናውኑት ነገር ነው በ27 ደቂቃ የጨመረው ስለዚህ የሞባይል ወደ ቤተሰብ ግንኙነት ውስጥ ሰርጎ መግባት አያጠራጥርም።

የጥናቱ አቅራቢዎች ብዙ ጥናት በበቂ ጊዜ ቢደረግ እውነታውን በደንብ መረደት ይቻላል ሲሉ አስተያየታቸውን አክለዋል።
በነገራችን ላይ አንድ በቅርብ የተሰራ ጥናት እንዳመለከተው ሁለት ዓመት እንኳን ሳይሞላቸው የቲቪ ወይም የስልክ ስክሪን የሚያዩ ልጆች በእጥፍ ጨምሯል።

Comments

Popular posts from this blog

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች