Listen more, speak less/ ብዙ አድምጡ ትንሽ አውሩ
7ቱ ብዙ ከማውራት የማድመጥ ጥቅሞች
በቀን ምን ያህል እናወራለን? እስኪ ስንቶቻችን ነን ሰው ሲናገር ከልብ ከማድመጥ ይልቅ እኛ ስንናገር እንዴት የበለጠ እንደምንደመጥ የምናስብ?
ለጥያቄዎቹ የኔ ብጤዎቹ መልስ ብዙም እንደማያስደስት ይታወቃል። አሁን አሁን በሰው ዘንድ እየተለመደ የመጣ አስተሳሰብ አለ። ለምሳሌ ብዙ የተናገረ ሀሳቡን በሰው ውስጥ በደንብ ያሰረፀ፣ እውቀት ያለው፣ አሸናፊ ሃሳብ ያቀረበ እየመሰለን ነው። ልክ እንደ ስፓርት ውድድር በጩኸት ያወራ እና ብዙ የተናገረ ያሸነፈ ይመስለናል። በሳይኮሎጂ ግን እንደውም በተቃራኒው ነው። ብዙ የሚናገር ትንሽ ጥቅም ሲያገኝ ትንሽ የሚናገር በእጅጉ ይጠቀማል። በሚከተሉት ምክንያቶች፦
- ዕውቀት ኀይል ነው፦ በዚህ ዘመን የምናውቀውን በመጨመር እንጂ በየአጋጣሚው በመዝራት እና በመጨረስ አሸናፊ አይኮንም።
- ባልተናገርኩ ኖሮ የሚያስበለን ይቀንሳል፦ ትንሽ መናገር በኋላ የሚቆጨንን ነገር እንዳንናገር ጊዜ ይሰጠናል።
- ፍሬ አልባ ነገር ከመናገር እንታቀባለን፦ አብርሃም ሊንከን እንዲህ ብሎ ነበር " በዝምታ ላይ ሰው ሞኝ ነው ብሎ እንዲያስብ ማድረግ ተናገርን ሞኝነታችንን እርግጠኛ እንዲሆኑ ከማድረግ ይበልጣል" እንዳለው ትንሽ በመናገር እርግጠኛና በቂ እውቀት ባለን ነገር ላይ መናገር።
- አቅማችንን እንቆጥባለን፦ መቼም የአንድ ሰው የዕውቀት ወይም ልምድ መጠን ትንሽ ነው። ስለዚህ ብዙ ማውራት ልክ መጀመሪያ ሮጦ ኀይሉን እንደጨረሰ አትሌት ነው። በኋላ ወሬያችን ሁሉ የተደጋገመና አሰልቺ ስለሚሆን ዝምተኛው ትንሽ አውርቶ ተደማጭነት ያገኛል።
- ብዙ የሚናገር ያሸነፈና ሰው የተረዳው ይመስለዋል፦ ሰውን ከልብ የምናደምጠው ከሆነ የተረዳነው ስለሚመስለው ትንሽ የምንናገር በመሆናችን የተሻለ ማህበራዊ ግንኙነት ይኖረናል።
- ሚስጥር ያወጣል፦ ብዙ የሚናገር ሚስጥር የማውጣት እድሉ ትንሽ ከሚያወራ የበለጠ መሆኑ የታወቀ ነው።
- ንግግራችንን ሰው ያደምጠዋል፦ ልክ እንደ ኢኮኖሚክስ የአቅርቦት እና ፍላጎት ህግ ነው። እስኪ እናስበው ሁል ጊዜ የሚያወራን ነው ወይስ አልፎ አልፎ ለሚያወራ ሰው ንግግር ትኩረት የምንሰጠው? አልፎ አልፎ የሚያወራ የሚናገረው ቃል ሁሉ በአጠገቡ ላሉ ሰዎች እንደልብ የማይገኝ ስለሆነ በስስት ይጠብቁታል።
Comments
Post a Comment