Wise women to look beautiful/ ቀላል የቁንጅና ብልሃቶች

የታወቁ ቆንጆ ሴቶች በብልሃት ተዋቡ ብለው የሚከተሉትን ብልሃቶች ይመክራሉ
በቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ መንከር
በአቅራቢያችሁ ጥፍር ቀለም ማድረቂያ ከሌለ እጃቹን ቀዝቀዝ ያለ ውሃ ዎስጥ መንከር በደንብ ይሰራል።
በጥፍር ዙሪያ መቀባት
በተለይ የጥፍር ቀለም ዲዛይን ስትሰሩ በጥፍሩ ዙሪያ የወይራ ዘይት መቀባት ያለምንም የቀለም መዝረክረክ ያማረ ቀለም ትቀባላቹ።
የሚያምር ቀለም በስቲም
በሚቀጥለው ስታበስሉ ወይም ውሃ ስታፈሉ ሁለት አይነት የጥፍር ቀለም ደራርባችሁ ቀቡ ከዛም ሳይደርቅ ከሚበስለው ነገር በሚወጣው እንፋሎት እንዲደርቅ አድርጉና ውበቱን ተመልከቱ።
ፋውንዴሽን ላይ ሌላ ከመደረብ
ፋውንዴሽንሽ እየሳሳ ከሄደ በግብዣ ላይ ወይም በመሳሰሉት ሌላ ፋውንዴሽን ከመደረብ በፊት ፈሳሽ ክሬም ቀስ ብሎ ጉንጭ ላይ ማድረግ ተጨማሪ ውበት ይፈጥራል።
አይንን በነጠብጣብ ማስዋብ
በጣም የሚከብደውን ወጥ መስመር ለመስራት ፈሳሹን ኩል ተጠቀሙና በዓይናቹ ሽፋሽፍት በኩሉ ጫፍ ሳይሆን ሰፋ በሚለው በኩል ላይ ቁጭ ብድግ ከዛም ትንሽ ጠጋ ብላችሁ ቁጭ ብድግ ከዛም እንደዛው ከሶስት ወይም አራት ጊዜ በኋላ ወጥ መስመር ትሰራላችሁ።
ከፍሪጅ አውጥቶ መቅረፅ
የአይን ኩላችሁ ወይም የከንፈር ከለራችሁ ስስት ብሎ ስትቀርፁት ብዙ የሚባክን ከሆነ ፍሪጅ ውስጥ ለአንድ ሰዓት አስቀምጡት።
ፊትሽን በክብ ቦርሺው
በተለይ ትንሽ ፀጉር ፊትሽ ላይ ካለ ብሩሽ ያዢና ከጉንጭሽ አጥንት እስከ የፀጉርሽ መጀመሪያ ትንሽ ክብ እየሰራሽ ብትቦርሺው እንከን የለሽ በንፋስ የተሰራ የሚመስል ቅርፅ ይሰጥሻል።
የኤ ቲ ኤም ወይም የቢዝነስ ካርድ መጠቀም
የበዛ ሽፋሽት ለማግኘት ካርዱን ከሽፋሽፍቱ ኋላ የአይንሽን ቆዳ ሸፍኖ እንዲቀመጥ አድርጊ ከዛም ከሽፋሽፍቱ ስር ጀምረሽ ያለምንም መሳቀቅ ወደላይ ካርዱን ጨምሮ ማስካራ መቀባት የማይታመን ውፍረትና ርዝመት ያለው ሽፋሽፍት ይሰጣል።
ላማረ ከርል ፀጉር እጅን ሰብሰብ
ፀጉር ከታጠቡ በኋላ በስስ ጨርቅ አድርቆ ኮንዲሽነር መቀባት በቃ ከዛ መተው ነው ፀጉሩ የራሱን መንገድ ተከትሎ ሲደርቅ በእጅ አስሬ እየነካኩ ከሚመጣው ውበት ይበልጣል።
ፎጣው ይቀመጥ
ፀጉርን ከሚጨርሰው ተግባር አንዱ በፎጣ ፀጉርን ማድረቅ ነው ይልቅ አሮጌ የሆነ ከለስላሳ ጥጥ የተሰራ ቲ ሸርት ተጠቅሞ ጫን ጫን እያሉ ማድረቅ ለፀጉር እንክብካቤ ይረዳል።

Comments

Post a Comment

Popular posts from this blog

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች