Work and Love/ ፍቅር ከስራ ጋር

ከስራ ባልደረባ ጋር ፍቅር እንዴት ነው?
ናታሻ ስራ የተቀጠረች ቀን ከማቲዎስ አጠገብ የሚገኝ ጠረጴዛ ላይ እንድትቀመጥ ሆነ። ' ገና እንዳየሁት ነው የወደድኩት' የምትለው ናታሻ ' ከጊዜ በኋላም ከሰላምታና አንድ አንድ ጊዜ ከማውራት በስተቀር ከስራ ውጭ እንገናኝ ምናምን ብሎኝ አያውቅም ስለዚህ እኔ እራሴ በጓደኛዬ ልደት ላይ ጋበዝኩትና ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳሳምን' ትላለች። ' ከዛማ በቃ ወሬያችን አብረን መሆናችን ለስራ ባልደረቦቻችን ፍቅር እንደጀመርን ማስታወቂያ ሆነ፣ በመሆኑም ከአመት የፍቅር ግንኙነት በኋላ ለማቋረጥ ስንወስን ሁለታችንም ቀለል ለማድረግ ብንወስንም የነበረው ሁኔታ ቀላል አልነበረም ደግነቱ ከሳምንት በኋላ ስራ ቀየርኩኝ እንጂ' ብላለች።

ናታሻ እንደ ምሳሌ የወሰድናት በጣም ብዙ ከስራ ባልደረባ ጋር ፍቅር የሚጀምሩ እንዳሉ ለማመልከት ሲሆን በአሜሪካ በተደረገ ጥናት መሰረት 27% ሰራተኞች የስራ ቦታን የፍቅር ጓደኛ ማግኛ አድርገው ሲቆጥሩ 15% ተጠያቂዎች ደግሞ ያሁኑ የትዳር ጓደኛቸውን አብረው ሲሰሩ እንደተዋወቁ ተናግረዋል።
' የስራ ጓደኛ ጋር ፍቅር ተጀምሮ ቢቋረጥ በየቀኑ መገናኘት ግድ ሲሆን ይጎዳል' የምትለው ካናዳዊ ሳይኮሎጂስት ' በዚህ ምክንያት የስራ ብቃታቸው የቀነሰ፣ ስራቸውን ለመልቀቅ የተዳረጉ ደንበኞች ነበሩኝ' ብላለች።

ሳይኮሎጂስቷ ኒኮል ማኬንስ እንደምትለው ሁለት ነገር ከግምት ማስገባት ይጠቅማል የስራ ባልደረባን ለፍቅር ስናስብ። አንደኛ ቀጣሪያችሁ ይህንን ግንኙነት የሚከለክል ህግ አለው የለውም የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከአለቃ ጋር ግንኙነት መመስረት በሌላው ሰራተኛ መጠመድን ካልተስማማቹ ደግሞ ስራ ማጣትን ሊያስከትል ስለሚችል አስቡበት ትላለች።

ኒኮል የሚከተሉትን ምክር ከስራ ባልደረባ ጋር ፍቅር ለጀመሩ አስቀምጣለች፦

  • የስራ ተነሳሽነታቹም ሆነ ሞራላቹ አይለወጥ
  • ለፍቅረኛቹ አታዳሉ
  • ለሌሎች ባልደረቦች መናገር አለመናገርን አብራቹ ወስኑ
  • ነገር ግን በምንም መልኩ የፍቅረኛቹን እንከን ከባልደረቦች ገር አተውሩ
  • በመጨረሻም ሁል ጊዜም የመለያየት እድል እንዳለ ከግምት ውስጥ ማስገባት ይጠቅማል ብላለች።

Comments

Popular posts from this blog

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች