Fight selfish people/ ራስ ወዳዶች ይጥ......


ለራስ ወዳድ ሰዎች የሚፈልጉትን በመስጠት ጊዜ ማቃጠል አያስፈልግም። ራስ ወዳድነት የተፈጥሮ ነገር ቢሆንም እኔ የማተኩረው በራስ ወዳድነታቸው የብዙዎችን ህይወት ስለሚያበላሹት ጥፋተኞች ነው። እነዚህ ሰዎች በልጅነታቸው በደረሰባቸው የስነልቦና ጫና ወይም ደግሞ ከጊዜ በኋላ አውቀው የሚያሳዩት ባህሪ ነው።
የሚከተሉት ፀባዬችንም ታዩባቸዋላችሁ፦
ያኮርፋሉ፦ በዚህም የነሱ ብቻ ነገር እንደሚሳካ ያምናሉ። ብዙ ግዜም ይሳካላቸዋል ምክንያቱም ይህንን ባህሪ የሚያሳዩት ለሚቀርቧቸው ሰዎች ስለሆነ።
እንዲታዘንላቸው ምክንያት አያጡም፦ ሁል ጊዜ አመመኝ፣ ሁል ጊዜ ተጠቃው በማለት የሚቀርቧቸውን ሰዎች ያስጨንቃሉ።

አስመሳይ ናቸው፦ የቅርብ ሰው ጋር ብቻቸውን ሲገናኙ አውሬ ይሆናሉ ሌላ ሰው ከተገኘ ግን መሬት ይሆናሉ እንዲህ በማድረግም ብዙ ልምድ አካብተዋል። ስለዚህ የቅርቡ ሰው ቢታዘባቸውም አይገዳቸውም ምክንያቱም በቁጥጥሬ ስር ነው ብለው ስለሚያምኑ።
በቀላሉ ይናደዳሉ፦ ሲናገሯቸው ቶሎ ይቆጣሉ።
የሰውን መሻሻል ይጠላሉ፦ የቅርብ ሰዋቸው ተሻሽሎ ከማየት ሞት ይመርጣሉ ምክንያቱም በነሱ ላይ ተረማምዶ የተሳካለት ስለሚመስላቸው።


Comments

Popular posts from this blog

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች