How to make your eyes beautiful/ የዓይን ሜክአኘ ቅደም ተከተል ላንቺ



እነዚህን ቅደም ተከተሎች በመተግበር የተዋበ ዓይን ይኑርሽ
1. ፋውንዴሽን 


የዓይንሽን ሽፋንሽን ፋውንዴሽን አድርጊበት፣ የዓይን ኘሪሚየር ካለሽ ከፋውንዴሽኑ በፊት መቀባት ትችያለሽ ነገር ግን እስኪደርቅ መጠበቅ አትርሺ።
2. ሻዶው


ከቆዳሽ ቀለም ነጣ ያለ ሻዶው መርጠሽ ፋውንዴሽኑ ላይ መቀባት።ከዛም ለቆዳሽ በግማሽ ንጣት ቀረብ ያለ ሻዶው ደርቢበት። ቀጥሎ የዓይንሽ ሽፋን ጫፍ በመከተል ከቆዳሽ ቀለም ጠቆር ያለ ሻዶው መቀባት።
3.በአይን ብሩሽ መጠቀም


የዓይን ብሩሽ በመጠቀም ከቆዳ ቀለምሽ ነጣ ያለውን ሻዶው ከዕቃውስጥ በመንካት በዓይንሽና አፍንጫሽ ኮርነር  በጥንቃቄ መቀባት። 
4.ቅንድብሽን መቀባት


ነጣ ያለውን ሻዶው ተጠቅመሽ የቅንድብሽን የታችኛው መሥመርን መቀባት። 
5. ጠቆር ያለውን ሻዶው መቀባት


ከአፍንጫሽ ኮርነር ጀምረሽ የዓይን አጥንትሽን በመከተል ወደጎን ጠቆር ያለውን ሻዶው መቀባት። ከዓይን አጥንትሽ በታች የሚገኘውና የዓይን ኳስሽ ሽፋን ግን ነጣ እንዳለ ይቆይ።
6.የታችኛውን የዓይን ሽፋን መቀባት




ከውጨኛው የዓይንሽ ጥግ ጀምረሽ ቅድም አፍንጫሽ ጥግ ላይ የተቀባሽው ነጣ ያለ ሻዶው ድረስ ጠቆር ያለውን ሻዶው መቀባት።
7.ኩል መቀባት


የዓይንሽን የውስጥ ሽፋን ተከትለሽ ከላይ በ6 ላይ የተቀባሽው ሻዶው ድረስ ኩል በመቀባት ማጠናቀቅ።
8. ከዛም ማስካራ፣ከዛም አርቴፊሻል የዓይን ሽፋሽፍት




Comments

Popular posts from this blog

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች