Cryptocurrency computer world/ ኮምፒውተር ዓለም
Cryptocurrency/ ክሪፕቶ ከረንሲ
ክሪፐቶ ከረንሲ/ክሪፕቶ/ኮይን ዲጅታል የገንዘብ ዓይነት ሲሆን የኮምፒውተር ኔትዎረክ (ግንኙነት) በመጠቀም በባንክ ፈንታ የዲጅታል የሂሳብ ቁዋት(ሌጀር ) በዲጅታል ማጠራቀሚያ(ዳታ ቤዝ) ውስጥ በማስቀመጥ (ልክ የባንክ ቡክ የያዘውን የገንዘብ መጠን እና ዝውውር እንደሚጠቁመው) የኮይኑን/ክሪፕቶውን ባለቤት በ ፕሩፍ ኦፍ ስቶክ(በክሪፕቶ ባለሀብቶች እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የተረጋገጠ መጠን ) የሚደገፍ የልውውጥ መንገድ ነው፡፡
ክሪፐቶ ከረንሲ ገና ሲሰራ(ሲታተም) በአንድ አካል ማዕከላዊነት(እንደ ብሄራዊ ባንክ) ቢሆንም ብሎክ ቼይን (ማንም ሊመለከተው የሚችል የክሪፕቶ ዝውውር መረጃ) ውስጥ የሂሳብ ቁዋቱ(ሌጀሩ) ከተሰራጨ በዋላ ማዕከላዊነቱን በማጣት በተመረቱት የኮይን ዝውውር ውስጥ የራሱን ልውውጥ ያከናውናል፡፡ ግለሰቦች ክሪፕቶ ሲያዘዋውሩ ማንነታቸው ሳይሆን የተለየ ስም ወይም አድራሻቸውን በማድረግ ራሳቸውን አለማሰወቅ የሚችሉ ቢሆንም የባለቤቶቹን ማንነት ግን በሚሰጥር መቆለፍ በሚችል ነገር ግን ለባለስልጣን የሚታወቅ እንዲሆን ህግ አውጪዎች ያሰገድዳሉ፡፡
Comments
Post a Comment