5 የፍቅር መጠቆሚያዎች



1. ወዳጃችን ስለኛ ብዙ ከማሰብ የተነሳ ማንኛውንም መንገድ ከኛጋር ለመገናኘት ይፈልጋል/ች፡፡ ለምሳሌ በሰበብ አስባቡ ወደእኛ ጋር መመላለስ፣ በጥዋት ወይም ከመሸ በዋላ ቴክስት መላክ፤

2. ከሰዎች ወይም ከጋራ ጉዋደኛ ጋር ስንሆን የተለየ ትኩረት የሚሰጠው/የምትሰጠው ከኛ ለሚመጣው ሀሳብ ይሆናል፡፡ ከኛ ተቃራኒ ሃሳብ የሚያቀርበውን ደግሞ እንደራሳችን ሆኖ/ና መተቸት፤

3. ከኛ ጋር ሲያወሩ የሚጠቀሙት ድምፅ ለስለስ ያለና የተረጋጋ ሆኖ ሲያወሩም ዓይን ዓይናችንን በማየት ነው፡፡ በስልክ ሲያወሩን ደግሞ አልፎ አልፎ እእእእ..... በማለት ድምፃቸውን ለማጥራት ይሞክራሉ፤

4. በቀጠሮ ለመገናኘት ከተስማማቹ ስትገናኙ ከወትሮው የተለየና አምሮባቸው ለመታየት ተጨማሪ ነገር አድርገው ታስተውላላቹ፡፡ ለምሳሌ ጎላ ያለ ሊፕስቲክ ወይም የሰውነት ቅርፃቸውን የሚያጎላ ልብስ ልትለብስ ትችላለች እሱ ደግሞ  ፀጉሩን በሚገባ አሳምሮ ሽቶ ወይም ሎሽን ተቀብቶ ይገኛል፤

5. አብራቹ ስትሆኑ ሙሉ ትኩረታቸውን ለእኛ ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ ስልካቸው ትዝም አይላቸውም፣ ድንገት ቢደወልላቸው እንኩዋን በአጭሩ በመቅጨት ትኩረታቸውን ወደ እኛ ይመልሳሉ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ሰባቱ ባህሪያት፤ ሰውነት!

5ቱ ከፍቅረኛ ጋር የማይወሩ ርዕሶች

የፍቅር 15 በጥናት የተረጋገጡ እውነታዎች