Posts

5 የፍቅር መጠቆሚያዎች

Image
1. ወዳጃችን ስለኛ ብዙ ከማሰብ የተነሳ ማንኛውንም መንገድ ከኛጋር ለመገናኘት ይፈልጋል/ች፡፡ ለምሳሌ በሰበብ አስባቡ ወደእኛ ጋር መመላለስ፣ በጥዋት ወይም ከመሸ በዋላ ቴክስት መላክ፤ 2. ከሰዎች ወይም ከጋራ ጉዋደኛ ጋር ስንሆን የተለየ ትኩረት የሚሰጠው/የምትሰጠው ከኛ ለሚመጣው ሀሳብ ይሆናል፡፡ ከኛ ተቃራኒ ሃሳብ የሚያቀርበውን ደግሞ እንደራሳችን ሆኖ/ና መተቸት፤ 3. ከኛ ጋር ሲያወሩ የሚጠቀሙት ድምፅ ለስለስ ያለና የተረጋጋ ሆኖ ሲያወሩም ዓይን ዓይናችንን በማየት ነው፡፡ በስልክ ሲያወሩን ደግሞ አልፎ አልፎ እእእእ..... በማለት ድምፃቸውን ለማጥራት ይሞክራሉ፤ 4. በቀጠሮ ለመገናኘት ከተስማማቹ ስትገናኙ ከወትሮው የተለየና አምሮባቸው ለመታየት ተጨማሪ ነገር አድርገው ታስተውላላቹ፡፡ ለምሳሌ ጎላ ያለ ሊፕስቲክ ወይም የሰውነት ቅርፃቸውን የሚያጎላ ልብስ ልትለብስ ትችላለች እሱ ደግሞ   ፀጉሩን በሚገባ አሳምሮ ሽቶ ወይም ሎሽን ተቀብቶ ይገኛል፤ 5. አብራቹ ስትሆኑ ሙሉ ትኩረታቸውን ለእኛ ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ ስልካቸው ትዝም አይላቸውም፣ ድንገት ቢደወልላቸው እንኩዋን በአጭሩ በመቅጨት ትኩረታቸውን ወደ እኛ ይመልሳሉ፡፡

ምዕራብ ፀሃይ መጥለቂያ እንጂ ህይወት መንጠቂያ አይደለም

ማሙሽና ቲሞ ማሙሽ፣ ምን እንደሚገርመኝ ታቃለህ? ቲሞ፣ ምን? ማሙሽ፣ ለምን ቲሞ እንደምንልህ? ቲሞ፣ ቲማቲም ባጭሩ ሲቆላመጥ ቲሞ ነው፡፡ ማሙሽ፣ ዛሬ ምን ብዬ ፖሰትኩኝ መሰለህ፣ ምዕራብ ፀሃይ መጥለቂያ እንጂ ህይወት መንጠቂያ አይደለም፡፡ ጥዋት ፀሃይ እየሞኩኝ እነ ማይካደራ፣ አበዱራፊ፣ መተማ፣ ቦርኒ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ጎቦ፣ ኮጎ ዳላ፣ ምናምን የሚኖሩ ወገኖቻችን ትዝ እያሉኝ ፀሃይ ሳትሰስት ለሁሉም ህይወት ለመሆን በምስራቅ ትወጣለች ክፉ ሰዎች በምዕራብ ህይወት ይነጠቃሉ አልኩና ለሰው አጋራው እልሃለው፡፡ ቲሞ፣ በጣም ያሳዝናል፣ ግንኮ መከላከያ ክፉዎቹን እያጨዳችው ነው፡፡ ሆን ተብሎ የብሄር ግጭት ለማስነሳት ኮ ነው፡፡ ማሙሽ፣ የብሄር ግጭት ለመነሳት የሚያስገድድ ነገር ሳይኖር መሆኑ እነዳልከው ሆን ተብሎ የሚሰራበት እና ሌላ ትርፍ ለማግኘት ነው፡፡ የራሱን ሰላማዊ ህይወት እየለፋ ከአካባቢው ጋር ተስማምቶና ተቻችሎ የሚኖር ዜጋ እንደዚህ አይነት ግፍ አይፈፀምበትም፡፡ እንኩዋን ኢትዮጵያ ሌሎች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያልዳበሩ ማህበረሰቦችም አያደርጉትም፡፡ ቲሞ፣ መንግስት ስራውን በትክክል እነዲሰራ ሰዉ ቢተባበር ጥሩ ነው፡፡ በተለይ እነዚህ ለምዕራብ ድንበር በቀረቡት ያገራችን ከተሞች፡፡ ማሙሽ፣ መንግስት እራሱ ለዚህ ጉዳይ በቂ ትኩረት ሰቶታል ወይ? አንዴ፣ ሁለቴ፣ሶሰቴ፣ ሲደጋገም የመንግስትን አካሄድ መጠራጠር እንዳይጀመር መጠንቀቅ ይበጃል፡፡ የሰው ደም ይጣራል፣ የስካሁኑ ይበቃል፡፡ ሃሳብን ሰብሰብ አድርጎ በቅን መንፈስ መፍትሄ እነዲመጣ ቀን ከሌት መልፋት ይጠበቅበታል መንግስት፡፡

Cryptocurrency computer world/ ኮምፒውተር ዓለም

Image
Cryptocurrency/ ክሪ ፕ ቶ ከረንሲ   ክሪፐቶ ከረንሲ/ክሪፕቶ/ኮይን ዲጅታል የገንዘብ ዓይነት ሲሆን የኮምፒውተር ኔትዎረክ (ግንኙነት) በመጠቀም በባንክ ፈንታ የዲጅታል የሂሳብ ቁዋት(ሌጀር ) በዲጅታል ማጠራቀሚያ(ዳታ ቤዝ) ውስጥ በማስቀመጥ (ልክ የባንክ ቡክ የያዘውን የገንዘብ መጠን እና ዝውውር እንደሚጠቁመው) የኮይኑን/ክሪፕቶውን   ባለቤት በ ፕሩፍ ኦፍ ስቶክ(በክሪፕቶ ባለሀብቶች እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የተረጋገጠ መጠን ) የሚደገፍ የልውውጥ መንገድ ነው፡፡ ክሪፐቶ ከረንሲ ገና ሲሰራ(ሲታተም) በአንድ አካል ማዕከላዊነት(እንደ ብሄራዊ ባንክ) ቢሆንም ብሎክ ቼይን (ማንም ሊመለከተው የሚችል የክሪፕቶ ዝውውር መረጃ) ውስጥ የሂሳብ ቁዋቱ(ሌጀሩ) ከተሰራጨ በዋላ ማዕከላዊነቱን በማጣት በተመረቱት የኮይን ዝውውር ውስጥ የራሱን ልውውጥ ያከናውናል፡፡   ግለሰቦች ክሪፕቶ ሲያዘዋውሩ   ማንነታቸው ሳይሆን የተለየ ስም ወይም አድራሻቸውን በማድረግ ራሳቸውን አለማሰወቅ የሚችሉ ቢሆንም የባለቤቶቹን ማንነት ግን በሚሰጥር መቆለፍ በሚችል ነገር ግን ለባለስልጣን የሚታወቅ እንዲሆን ህግ አውጪዎች ያሰገድዳሉ፡፡

The New birr/ አዲሱ ብር

Image
ከብሩ ጋር የተለወጡ 1. ከፍተኛው የብር ኖት ፦ ከ መቶ ወደ ሁለት መቶ ማደጉ የብሩን ዝውውር ይቀንሳል ተብሎ ይታመናል። የ መቶ ብር ዝውውር ግን ከ በፊቱም ይጨምራል። 2. የብር ኖቶቹ ቀለም ፦ ከቀለማቸው ጋር የ ትክክለኛነት ማረጋገጫዎቹ መጨመርና መዘመን የአዲሶቹን ብር ዋጋ ከፍ ያለ ያደርጋቸዋል። 3. ለብሮቹ ማሳተሚያ የወጣው ወጪ ፦ ብርን ለማተም የሚወጣው ወጪ የብሩን ዋጋ ከፍ ያደርገዋል።  4. ያልተለወጠው አምስት ብር ፦ ስላልተለወጠ ዋጋውም ሆነ ስርጭቱ እንደ በፊቱ ይቀጥላል። 5. የባንኮች ወለድ ፦ ባንኮች የወለድ መጠናቸውን ባይቀይሩም የብር ኖቶቹ መቀየር ከሚያመጣው የድሮና የተለወጠው ብር ዋጋ ስለሚለያይ የተጨማሪ እሴት ተጠቃሚ ናቸው።

How to make your eyes beautiful/ የዓይን ሜክአኘ ቅደም ተከተል ላንቺ

Image
እነዚህን ቅደም ተከተሎች በመተግበር የተዋበ ዓይን ይኑርሽ 1. ፋውንዴሽን   የዓይንሽን ሽፋንሽን ፋውንዴሽን አድርጊበት፣ የዓይን ኘሪሚየር ካለሽ ከፋውንዴሽኑ በፊት መቀባት ትችያለሽ ነገር ግን እስኪደርቅ መጠበቅ አትርሺ። 2. ሻዶው ከቆዳሽ ቀለም ነጣ ያለ ሻዶው መርጠሽ ፋውንዴሽኑ ላይ መቀባት።ከዛም ለቆዳሽ በግማሽ ንጣት ቀረብ ያለ ሻዶው ደርቢበት። ቀጥሎ የዓይንሽ ሽፋን ጫፍ በመከተል ከቆዳሽ ቀለም ጠቆር ያለ ሻዶው መቀባት። 3. በአይን ብሩሽ መጠቀም የዓይን ብሩሽ በመጠቀም ከቆዳ ቀለምሽ ነጣ ያለውን ሻዶው ከዕቃውስጥ በመንካት በዓይንሽና አፍንጫሽ ኮርነር  በጥንቃቄ መቀባት።  4. ቅንድብሽን መቀባት ነጣ ያለውን ሻዶው ተጠቅመሽ የቅንድብሽን የታችኛው መሥመርን መቀባት።  5. ጠቆር ያለውን ሻዶው መቀባት ከአፍንጫሽ ኮርነር ጀምረሽ የዓይን አጥንትሽን በመከተል ወደጎን ጠቆር ያለውን ሻዶው መቀባት። ከዓይን አጥንትሽ በታች የሚገኘውና የዓይን ኳስሽ ሽፋን ግን ነጣ እንዳለ ይቆይ። 6. የታችኛውን የዓይን ሽፋን መቀባት ከውጨኛው የዓይንሽ ጥግ ጀምረሽ ቅድም አፍንጫሽ ጥግ ላይ የተቀባሽው ነጣ ያለ ሻዶው ድረስ ጠቆር ያለውን ሻዶው መቀባት። 7. ኩል መቀባት የዓይንሽን የውስጥ ሽፋን ተከትለሽ ከላይ በ6 ላይ የተቀባሽው ሻዶው ድረስ ኩል በመቀባት ማጠናቀቅ። 8. ከዛም ማስካራ፣ከዛም አርቴፊሻል የዓይን ሽፋሽፍት ።

Fight selfish people/ ራስ ወዳዶች ይጥ......

Image
ለራስ ወዳድ ሰዎች የሚፈልጉትን በመስጠት ጊዜ ማቃጠል አያስፈልግም። ራስ ወዳድነት የተፈጥሮ ነገር ቢሆንም እኔ የማተኩረው በራስ ወዳድነታቸው የብዙዎችን ህይወት ስለሚያበላሹት ጥፋተኞች ነው። እነዚህ ሰዎች በልጅነታቸው በደረሰባቸው የስነልቦና ጫና ወይም ደግሞ ከጊዜ በኋላ አውቀው የሚያሳዩት ባህሪ ነው። የሚከተሉት ፀባዬችንም ታዩባቸዋላችሁ፦ • ያኮርፋሉ ፦ በዚህም የነሱ ብቻ ነገር እንደሚሳካ ያምናሉ። ብዙ ግዜም ይሳካላቸዋል ምክንያቱም ይህንን ባህሪ የሚያሳዩት ለሚቀርቧቸው ሰዎች ስለሆነ። • እንዲታዘንላቸው ምክንያት አያጡም ፦ ሁል ጊዜ አመመኝ፣ ሁል ጊዜ ተጠቃው በማለት የሚቀርቧቸውን ሰዎች ያስጨንቃሉ። • አስመሳይ ናቸው ፦ የቅርብ ሰው ጋር ብቻቸውን ሲገናኙ አውሬ ይሆናሉ ሌላ ሰው ከተገኘ ግን መሬት ይሆናሉ እንዲህ በማድረግም ብዙ ልምድ አካብተዋል። ስለዚህ የቅርቡ ሰው ቢታዘባቸውም አይገዳቸውም ምክንያቱም በቁጥጥሬ ስር ነው ብለው ስለሚያምኑ። • በቀላሉ ይናደዳሉ፦ ሲናገሯቸው ቶሎ ይቆጣሉ። • የሰውን መሻሻል ይጠላሉ ፦ የቅርብ ሰዋቸው ተሻሽሎ ከማየት ሞት ይመርጣሉ ምክንያቱም በነሱ ላይ ተረማምዶ የተሳካለት ስለሚመስላቸው።

Do you want to start a business?/ ንግድ ላይ ኖት?

ንግድ መጀመር አስበዋል? ንግድ ማለት ለህብረተሰብ ጠቃሚ የሆነ ምርት ወይም አገልግሎት ትርፍ ለማግኘት ሲባል የሚሰራ ማንኛውም ስራ ነው። ትርፍ ማለት ጠቃሚ ምርት ወይም አገልግሎት በማግኘቱ ህብረተሰቡ የሚሸልመው ሽልማት ነው። ነጋዴ ማለት ያለውን እውቀት፣ ኀብት ወይም ጊዜ ለንግድ የሚያቀርብ ግለሰብ ነው። በሌላ አነጋገር ማንኛውም በስራ ላይ የሚገኝ ሰው ነጋዴ ነው ማለት ነው። ስለዚህ በስራ ላይ ካሉ ንግድ ላይ ኖት ማለት ነው።