Tiger; the human killer/ ሰው በሊታው ነብር
436 ሰዎች የገደለው ነብሮ በልጅነቱ ያልተሳካለት አዳኝ አቁስሎ ያመለጠው ነብር አደገ። ነገር ግን በአዳኙ በደረሰበት አደጋ ሁለት የክራንቻ ጥርሶቹን አቷል። በዚህም ምክንያት እንደፈለገ የዱር እንስሳትን እያደነ መመገብ አልቻለም። በኔፓል እና ህንድ አዋሳኝ አካባቢዎች ሰዎች ደንን በመመንጠር እና በማረስ ይተዳደራሉ። ይህም በደን ውስጥ ከሚገኙ አውሬዎች ጋር ተቀራርበው እንደውም አንዳንዴም የተፈጥሮን ፀጋ ተጋርተው ይኖራሉ። ይህም ለአራዊቱ ምቾት ስለሚነሳ በብዛት መሰደዳቸው የማይቀር ነው። ስለዚህ አድነው የሚኖሩ እንስሳትም የምግብ እጥረት ተከስቶባቸዋል። አንድም በጥርሱ ምክንያት ቀጥሎም በአራዊቱ መመናመን የተቸገረው ነብር ደካማና በቀላሉ የሚገለው አደን ያደረገው የሰው ልጅን ይሆናል። በተለይ ሴቶችንና ህፃናትን እየመረጠ የዕለት ምግብ አደረጋቸው። በመሳሪያ እንዳይገሉት እንግሊዞች መሳሪያ ከልክለዋል። ነብሩ የሚያጠቃው ቦታና ጊዜም በውል የማይታወቅ ሆነ በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ የታወቀ ብቻ 436 ሰው መግደሉና መመገቡ የተረጋገጠው። በመጨረሻ ግን ነብርና አቦሸማኔ በማደንና በመግደል ታዋቂ ሰው ተቀጥሮ በብዙ ፈተና ሊገደል የቻለው።