Posts

Cryptocurrency computer world/ ኮምፒውተር ዓለም

Image
Cryptocurrency/ ክሪ ፕ ቶ ከረንሲ   ክሪፐቶ ከረንሲ/ክሪፕቶ/ኮይን ዲጅታል የገንዘብ ዓይነት ሲሆን የኮምፒውተር ኔትዎረክ (ግንኙነት) በመጠቀም በባንክ ፈንታ የዲጅታል የሂሳብ ቁዋት(ሌጀር ) በዲጅታል ማጠራቀሚያ(ዳታ ቤዝ) ውስጥ በማስቀመጥ (ልክ የባንክ ቡክ የያዘውን የገንዘብ መጠን እና ዝውውር እንደሚጠቁመው) የኮይኑን/ክሪፕቶውን   ባለቤት በ ፕሩፍ ኦፍ ስቶክ(በክሪፕቶ ባለሀብቶች እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የተረጋገጠ መጠን ) የሚደገፍ የልውውጥ መንገድ ነው፡፡ ክሪፐቶ ከረንሲ ገና ሲሰራ(ሲታተም) በአንድ አካል ማዕከላዊነት(እንደ ብሄራዊ ባንክ) ቢሆንም ብሎክ ቼይን (ማንም ሊመለከተው የሚችል የክሪፕቶ ዝውውር መረጃ) ውስጥ የሂሳብ ቁዋቱ(ሌጀሩ) ከተሰራጨ በዋላ ማዕከላዊነቱን በማጣት በተመረቱት የኮይን ዝውውር ውስጥ የራሱን ልውውጥ ያከናውናል፡፡   ግለሰቦች ክሪፕቶ ሲያዘዋውሩ   ማንነታቸው ሳይሆን የተለየ ስም ወይም አድራሻቸውን በማድረግ ራሳቸውን አለማሰወቅ የሚችሉ ቢሆንም የባለቤቶቹን ማንነት ግን በሚሰጥር መቆለፍ በሚችል ነገር ግን ለባለስልጣን የሚታወቅ እንዲሆን ህግ አውጪዎች ያሰገድዳሉ፡፡

The New birr/ አዲሱ ብር

Image
ከብሩ ጋር የተለወጡ 1. ከፍተኛው የብር ኖት ፦ ከ መቶ ወደ ሁለት መቶ ማደጉ የብሩን ዝውውር ይቀንሳል ተብሎ ይታመናል። የ መቶ ብር ዝውውር ግን ከ በፊቱም ይጨምራል። 2. የብር ኖቶቹ ቀለም ፦ ከቀለማቸው ጋር የ ትክክለኛነት ማረጋገጫዎቹ መጨመርና መዘመን የአዲሶቹን ብር ዋጋ ከፍ ያለ ያደርጋቸዋል። 3. ለብሮቹ ማሳተሚያ የወጣው ወጪ ፦ ብርን ለማተም የሚወጣው ወጪ የብሩን ዋጋ ከፍ ያደርገዋል።  4. ያልተለወጠው አምስት ብር ፦ ስላልተለወጠ ዋጋውም ሆነ ስርጭቱ እንደ በፊቱ ይቀጥላል። 5. የባንኮች ወለድ ፦ ባንኮች የወለድ መጠናቸውን ባይቀይሩም የብር ኖቶቹ መቀየር ከሚያመጣው የድሮና የተለወጠው ብር ዋጋ ስለሚለያይ የተጨማሪ እሴት ተጠቃሚ ናቸው።

How to make your eyes beautiful/ የዓይን ሜክአኘ ቅደም ተከተል ላንቺ

Image
እነዚህን ቅደም ተከተሎች በመተግበር የተዋበ ዓይን ይኑርሽ 1. ፋውንዴሽን   የዓይንሽን ሽፋንሽን ፋውንዴሽን አድርጊበት፣ የዓይን ኘሪሚየር ካለሽ ከፋውንዴሽኑ በፊት መቀባት ትችያለሽ ነገር ግን እስኪደርቅ መጠበቅ አትርሺ። 2. ሻዶው ከቆዳሽ ቀለም ነጣ ያለ ሻዶው መርጠሽ ፋውንዴሽኑ ላይ መቀባት።ከዛም ለቆዳሽ በግማሽ ንጣት ቀረብ ያለ ሻዶው ደርቢበት። ቀጥሎ የዓይንሽ ሽፋን ጫፍ በመከተል ከቆዳሽ ቀለም ጠቆር ያለ ሻዶው መቀባት። 3. በአይን ብሩሽ መጠቀም የዓይን ብሩሽ በመጠቀም ከቆዳ ቀለምሽ ነጣ ያለውን ሻዶው ከዕቃውስጥ በመንካት በዓይንሽና አፍንጫሽ ኮርነር  በጥንቃቄ መቀባት።  4. ቅንድብሽን መቀባት ነጣ ያለውን ሻዶው ተጠቅመሽ የቅንድብሽን የታችኛው መሥመርን መቀባት።  5. ጠቆር ያለውን ሻዶው መቀባት ከአፍንጫሽ ኮርነር ጀምረሽ የዓይን አጥንትሽን በመከተል ወደጎን ጠቆር ያለውን ሻዶው መቀባት። ከዓይን አጥንትሽ በታች የሚገኘውና የዓይን ኳስሽ ሽፋን ግን ነጣ እንዳለ ይቆይ። 6. የታችኛውን የዓይን ሽፋን መቀባት ከውጨኛው የዓይንሽ ጥግ ጀምረሽ ቅድም አፍንጫሽ ጥግ ላይ የተቀባሽው ነጣ ያለ ሻዶው ድረስ ጠቆር ያለውን ሻዶው መቀባት። 7. ኩል መቀባት የዓይንሽን የውስጥ ሽፋን ተከትለሽ ከላይ በ6 ላይ የተቀባሽው ሻዶው ድረስ ኩል በመቀባት ማጠናቀቅ። 8. ከዛም ማስካራ፣ከዛም አርቴፊሻል የዓይን ሽፋሽፍት ።

Fight selfish people/ ራስ ወዳዶች ይጥ......

Image
ለራስ ወዳድ ሰዎች የሚፈልጉትን በመስጠት ጊዜ ማቃጠል አያስፈልግም። ራስ ወዳድነት የተፈጥሮ ነገር ቢሆንም እኔ የማተኩረው በራስ ወዳድነታቸው የብዙዎችን ህይወት ስለሚያበላሹት ጥፋተኞች ነው። እነዚህ ሰዎች በልጅነታቸው በደረሰባቸው የስነልቦና ጫና ወይም ደግሞ ከጊዜ በኋላ አውቀው የሚያሳዩት ባህሪ ነው። የሚከተሉት ፀባዬችንም ታዩባቸዋላችሁ፦ • ያኮርፋሉ ፦ በዚህም የነሱ ብቻ ነገር እንደሚሳካ ያምናሉ። ብዙ ግዜም ይሳካላቸዋል ምክንያቱም ይህንን ባህሪ የሚያሳዩት ለሚቀርቧቸው ሰዎች ስለሆነ። • እንዲታዘንላቸው ምክንያት አያጡም ፦ ሁል ጊዜ አመመኝ፣ ሁል ጊዜ ተጠቃው በማለት የሚቀርቧቸውን ሰዎች ያስጨንቃሉ። • አስመሳይ ናቸው ፦ የቅርብ ሰው ጋር ብቻቸውን ሲገናኙ አውሬ ይሆናሉ ሌላ ሰው ከተገኘ ግን መሬት ይሆናሉ እንዲህ በማድረግም ብዙ ልምድ አካብተዋል። ስለዚህ የቅርቡ ሰው ቢታዘባቸውም አይገዳቸውም ምክንያቱም በቁጥጥሬ ስር ነው ብለው ስለሚያምኑ። • በቀላሉ ይናደዳሉ፦ ሲናገሯቸው ቶሎ ይቆጣሉ። • የሰውን መሻሻል ይጠላሉ ፦ የቅርብ ሰዋቸው ተሻሽሎ ከማየት ሞት ይመርጣሉ ምክንያቱም በነሱ ላይ ተረማምዶ የተሳካለት ስለሚመስላቸው።

Do you want to start a business?/ ንግድ ላይ ኖት?

ንግድ መጀመር አስበዋል? ንግድ ማለት ለህብረተሰብ ጠቃሚ የሆነ ምርት ወይም አገልግሎት ትርፍ ለማግኘት ሲባል የሚሰራ ማንኛውም ስራ ነው። ትርፍ ማለት ጠቃሚ ምርት ወይም አገልግሎት በማግኘቱ ህብረተሰቡ የሚሸልመው ሽልማት ነው። ነጋዴ ማለት ያለውን እውቀት፣ ኀብት ወይም ጊዜ ለንግድ የሚያቀርብ ግለሰብ ነው። በሌላ አነጋገር ማንኛውም በስራ ላይ የሚገኝ ሰው ነጋዴ ነው ማለት ነው። ስለዚህ በስራ ላይ ካሉ ንግድ ላይ ኖት ማለት ነው።

Tiger; the human killer/ ሰው በሊታው ነብር

Image
436 ሰዎች የገደለው ነብሮ በልጅነቱ ያልተሳካለት አዳኝ አቁስሎ ያመለጠው ነብር አደገ። ነገር ግን በአዳኙ በደረሰበት አደጋ ሁለት የክራንቻ ጥርሶቹን አቷል። በዚህም ምክንያት እንደፈለገ የዱር እንስሳትን እያደነ መመገብ አልቻለም። በኔፓል እና ህንድ አዋሳኝ አካባቢዎች ሰዎች ደንን በመመንጠር እና በማረስ ይተዳደራሉ። ይህም በደን ውስጥ ከሚገኙ አውሬዎች ጋር ተቀራርበው እንደውም አንዳንዴም የተፈጥሮን ፀጋ ተጋርተው ይኖራሉ። ይህም ለአራዊቱ ምቾት ስለሚነሳ በብዛት መሰደዳቸው የማይቀር ነው። ስለዚህ አድነው የሚኖሩ እንስሳትም የምግብ እጥረት ተከስቶባቸዋል። አንድም በጥርሱ ምክንያት ቀጥሎም በአራዊቱ መመናመን የተቸገረው ነብር ደካማና በቀላሉ የሚገለው አደን ያደረገው የሰው ልጅን ይሆናል። በተለይ ሴቶችንና ህፃናትን እየመረጠ የዕለት ምግብ አደረጋቸው። በመሳሪያ እንዳይገሉት እንግሊዞች መሳሪያ ከልክለዋል። ነብሩ የሚያጠቃው ቦታና ጊዜም በውል የማይታወቅ ሆነ በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ የታወቀ ብቻ 436 ሰው መግደሉና መመገቡ የተረጋገጠው። በመጨረሻ ግን ነብርና አቦሸማኔ በማደንና በመግደል ታዋቂ ሰው ተቀጥሮ በብዙ ፈተና ሊገደል የቻለው።

Listen more, speak less/ ብዙ አድምጡ ትንሽ አውሩ

Image
7ቱ ብዙ ከማውራት የማድመጥ ጥቅሞች በቀን ምን ያህል እናወራለን? እስኪ ስንቶቻችን ነን ሰው ሲናገር ከልብ ከማድመጥ ይልቅ እኛ ስንናገር እንዴት የበለጠ እንደምንደመጥ የምናስብ?  ለጥያቄዎቹ የኔ ብጤዎቹ መልስ ብዙም እንደማያስደስት ይታወቃል። አሁን አሁን በሰው ዘንድ እየተለመደ የመጣ አስተሳሰብ አለ። ለምሳሌ ብዙ የተናገረ ሀሳቡን በሰው ውስጥ በደንብ ያሰረፀ፣ እውቀት ያለው፣ አሸናፊ ሃሳብ ያቀረበ እየመሰለን ነው። ልክ እንደ ስፓርት ውድድር በጩኸት ያወራ እና ብዙ የተናገረ ያሸነፈ ይመስለናል። በሳይኮሎጂ ግን እንደውም በተቃራኒው ነው። ብዙ የሚናገር ትንሽ ጥቅም ሲያገኝ ትንሽ የሚናገር በእጅጉ ይጠቀማል። በሚከተሉት ምክንያቶች፦ ዕውቀት ኀይል ነው፦ በዚህ ዘመን የምናውቀውን በመጨመር እንጂ በየአጋጣሚው በመዝራት እና በመጨረስ አሸናፊ አይኮንም። ባልተናገርኩ ኖሮ የሚያስበለን ይቀንሳል፦ ትንሽ መናገር በኋላ የሚቆጨንን ነገር እንዳንናገር ጊዜ ይሰጠናል። ፍሬ አልባ ነገር ከመናገር እንታቀባለን፦ አብርሃም ሊንከን እንዲህ ብሎ ነበር " በዝምታ ላይ ሰው ሞኝ ነው ብሎ እንዲያስብ ማድረግ ተናገርን ሞኝነታችንን እርግጠኛ እንዲሆኑ ከማድረግ ይበልጣል" እንዳለው ትንሽ በመናገር እርግጠኛና በቂ እውቀት ባለን ነገር ላይ መናገር። አቅማችንን እንቆጥባለን፦ መቼም የአንድ ሰው የዕውቀት ወይም ልምድ መጠን ትንሽ ነው። ስለዚህ ብዙ ማውራት ልክ መጀመሪያ ሮጦ ኀይሉን እንደጨረሰ አትሌት ነው። በኋላ ወሬያችን ሁሉ የተደጋገመና አሰልቺ ስለሚሆን ዝምተኛው ትንሽ አውርቶ ተደማጭነት ያገኛል። ብዙ የሚናገር ያሸነፈና ሰው የተረዳው ይመስለዋል፦ ሰውን ከልብ የምናደምጠው ከሆነ የተረዳነው ስለሚመስለው ትንሽ የምንናገር በመሆናችን የተሻለ ማህበራዊ ግ...